የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ተግባር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!ሣውላ፦ጥር 27/2018 ዓ/ም
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት 6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ከሥር መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የቀጣይ ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫ የማስቀመጥ መድረክ አካሂዷል።
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ እንደተናገሩት መምሪያው የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የ5 ዓመት መሪ ዕቅዶችን ከልሶ ተግባራትን እየሰራ ይገኛል በማለት ገልፀዋል።
መሪ ዕቅድን መነሻ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊመብቶችን ለማክበርና ለማስከበር እንዲሁም መብትና ግዴታውን ጠንቅቆ የሚያቅ ህብረተሰብ ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመቀጠልም በዋና ዋና ዘርፎች በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዩች ፤የሴቶችና ህፃናት ልዩ ምርመራ ክስ ጉዳዮች ታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች የሙስና ወንጀል ጉዳዮች መንግስት የከሰሰባቸው የፍትሃብሄር ጉዳዮችን ለይቶ በጥብቅ ድስፕሊን በመሰራቱ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
በመደበኛ ፍርድ ቤት የተደረጉ የቀጥታ መደበኛ ክስ ክርክር ክትትል የሚቀርቡ ክሶችን በመመርመር ቀልጣፋና አፋጣኝ ውሳኔዎችን በመስጠት አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በፍትሐብሄር ጉዳዮች መንግስት ክሶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት 7,294,384 ብር በማስመለስ ውጤታማ ስራ መስራቱን ተናግሯል።
በፍትሐብሄር ጉዳዮች መንግስት የተከሰሰባቸውን ጉዳዮች ላይ በዐቃቤ ህግ መሰረት በመካሰስ ተገቢውን ክርክር በማድረግ መመለስ ያለበትን በመመለስ መንግስት መክፈል የሚገባውን እንዲከፍል ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች እጅግ ጫፍ የወጡ የመሬት ወረራዎችን በተመለከተ በጣም ፈታኝና የመሬት አስተዳደርን መሰረት አድርጎ አሰጣጡም ሆነ አወሳሰዱም ህጋዊ እንዲሆኑ ከግንዛቤ መፍጠር ጀምሮ መሬትን የማስመለስ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ተወካይና አቶ ለማላ አብርሃም በየፍርድ ቤቱ በመንግስት በኩል የሚከሰሱ ክሶችን በተገቢው መንገድ ውሳኔ እንዲያገኙ ዐቃቤያነ ህጎች በመረጃና በማስረጃ ግልፅ አቀራረብ በመጠቀም ማስፈፀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በፍትህ ስርዓቱ ላይ መፈታትና በቁርጠኝነት ሊሰሩ የሚገቡ በተለይ ተከሳሽ በጊዜ የማቅረብና የተሳለጠ ቀልጣፋ ስራ እንዲሰራ የማድረግ ስራን በይበልጥ መስራት ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል።
በመጨረሻም የተግባር አፈፃፀም ሰነድ ቀርቦ የጋራ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊ አካላት ሃሳብ አስተያዬት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።











