Deputy Head of Office and Head of legal affairs

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ  መልዕክት

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

በእውቀትና በጥናት ላይ የተመሰረተ የፍትህ ስርዓት ለጠንካራ ማህበረሰብ!

የፍትህ ስርዓት ውጤታማነቱ የሚለካው ህግን ከመተግበር ባለፈ፣ ጥራት ያላቸው ህጎችን በማውጣትና ማህበረሰቡ ስለ ህጉ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ነው። የዘርፋችን ዋነኛ ተልዕኮ የክልላችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ ህጎችን ማርቀቅ፣ የህግ ክፍተቶችን በጥናት መለየትና ዜጎች መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ነው።

ዘርፋችን በዋናነት በሚከተሉት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡-

 * የህግ ማርቀቅና ማሻሻል፡- የክልላችንን ልማትና ሰላም የሚደግፉ፣ ግልጽና ተራማጅ የሆኑ ህጎችን በማርቀቅ ረገድ በባለቤትነት እንሰራለን። ይህም በህግ አውጪውና በአስፈጻሚው መካከል የተሳለጠ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ያደርጋል።

 * የህግ ጥናትና ምርምር፡- የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡን የሚያቀጭጩ ችግሮችን በጥናት በመለየት፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን እናመነጫለን። አሰራሮቻችን ከባህላዊ ወደ ሳይንሳዊ መንገድ እንዲሸጋገሩ እናደርጋለን።

 * የህግ ግንዛቤ መፍጠር፡- ህግን የሚያከብር ማህበረሰብ ሊገነባ የሚችለው ዜጎች ስለ ህጉ በቂ እውቀት ሲኖራቸው ነው። በመሆኑም በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የህግ ትምህርት ለህዝባችን ተደራሽ በማድረግ የወንጀል ስጋቶችን እንቀንሳለን።

 * አቅም ግንባታና ስልጠና፡- በየደረጃው ለሚገኙ የፍትህ አካላትና የህግ ባለሙያዎች ወቅታዊና ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት፣ የሙያ ብቃታቸውንና የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እናሳድጋለን።

ባጠቃላይ ዘርፋችን የፍትህ ቢሮው የዕውቀትና የፖሊሲ ምንጭ በመሆን፣ በክልላችን የህግ የበላይነት እንዲሰፍንና ዜጎች በህግ ጥላ ስር ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ የማይተካ ሚና ይጫወታል።

ዘርፉ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች ለማስከበር እና ቀልጣፋ የሰነዶች ማረጋገጫ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በዚህም መሰረት፦

* ​የጠበቆች አገልግሎት፡ ጠበቆች በሙያ ስነ-ምግባር የታነፀ አገልግሎት እንዲሰጡ ክትትልና ድጋፍ እናደርጋለን።

* ​የሲቪክ ማህበራት ምዝገባ፣ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ፡ የሲቭከ ማህበራት ለሀገር ግንባታ እና ለዲሞክራሲ ስርዓት መጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ምቹ ሁኔታዎችን እንፈጥራለን፤ የምዝገባ፣ የድጋፍ፣ የክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ጥፋት ሲኖር ሕጋዊ እርምጃ እንወስዳለን።

* ​የሰነዶች ማረጋገጥ፡ ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት፣ ከማጭበርበር የጸዳ የሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ አገልግሎት እንሰጣለን።

* ​ሰብአዊ መብትና ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፡ የዜጎችን ሰብአዊ መብት በማስከበር እና አሰቃቂውን የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንሰራለን።

“ህግን ማወቅ ራስንና ሀገርን መጠበቅ ነው!”