lawyers:directorate of civil societies and registration of documents

የጠበቆች፣ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሰነድ ምዝገባና ማረጋገጫ ዳይሬክቶሪት

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

ዳይረክቶረቱ በፍትህ ቢሮ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 12/2016 አንቀፅ 8 የተሰጡትን ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ስራ ላይ የሚያውል ሲሆን በውስጡ ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን ያከናውናል፡፡ እነሱም፤

1ኛ. የጠበቆች አስተዳደር በተመለከተ፤

በክልሉ ለሚሰሩ ጠበቆች ጥብቅና ፈቃድ መስጠት፤ ፈቃዳቸውን በየዓመቱ ማደስ፤ ስጠፋ/ስበላሽ ድጋሜ መስጠት፤ የተለያዩ ድጋፍ ደብዳቤዎችን ለጠበቆች መስጠት እና ጠበቆች በመልካም ሥነ-ምግባር ሥራቸውን መስራታቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር እርምት እርምጃ መውሰድ፡፡

2ኛ. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር በተመለከተ፤

በክልሉ ለሚሰሩ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት፤ ፈቃዳቸውን ማደስ፤ ስጠፋ/ስበላሽ ድጋሜ መስጠት፤ የተለያዩ ድጋፍ ደብዳቤዎችን ለድርጅቶቹ መስጠት እና የትኛውም በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሲ.ማ.ድ በተቋቋሙበት ዓላማ እና በሀገርቱ ህግ መሰረት ሥራቸውን መስራታቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር እርምት እርምጃ መውሰድ፡፡

3ኛ. ሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ በተመለከተ፡

የትኛውም በክልሉ የሚመነጩ ሰነዶችን፤ ውሎችን እና ለሎችን እንድረጋገጡ የሚቀርቡ ሰነዶችን በህግ መሰረት መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ መመዝገብ ሲሆን ለሎች ከቢሮ የሚሰጡ ተግባራትን ያከናውናል፡፡