head of the justice bureau





የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

ተግባርና ኃላፊነቶች፡-

  • በአስፈፃሚ መስሪያቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 3/2016 አንቀፅ 16  እና የፍትህ ቢሮን ለማደራጀት፤ ሥልጣንና ተግባሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 12/2016 አንቀጽ 9 የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት እንዳለ ሆኖ መ/ቤቱን አስመልክቶ ስትራቴጂያዊ አመራር ይሰጣል፤
  • የተቋሙ ሰው ሀይል በአመለካከትና በክህሎት የሚታዩትን ክፍተቶች በመወያየት የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥና በመቅረፍ ለውጤት ያበቃል፣
  • የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ቀጣይነት ባለው መልኩ ውጤታማ እንዲሆን ይከታተላል፣
  •  የተቋሙን የለውጥ እንቅስቃሴ ይመራል፣በወቅቱ አፈፃፀሙን እየገመገመ አቅጣጫ ያስቀምጣል፤
  • የመስሪያ ቤቱ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማውጣት የሚቀርቡ ሪፖርቶችን ያፀድቃል፣
  •  የመስሪያ ቤቱ ዕቅድ አፈፃጸም ወቅቱን ጠብቆ በወር በ3ወር ፣ በ6 ወር በ9 ወር እና በዓመት እንዲገመገም ያደርጋል፤
  • በመስሪያ ቤቱ ተፈፃሚ የሚሆኑ ዝርዝር መመሪያዎች በማውጣት እንዲፀድቁ ያደርጋል /ያጸድቃል/፤
  • አጠቃላይ የተቋሙን ስራ ያስተባብራ ፣ይመራል፣
  • በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ያሉ አደረጃጀቶችን በበላይነት  ይመራል፤
  • ለፍትህ ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት ያስተባብራል፣ ይደግፋል፣ይመራል፤

1. የፍትህ ቢሮ የዘርፎች አደረጃጀት

በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ስር  ለፍትህ ቢሮ ኃላፊ ተጠሪ የሆኑ ሶስት የዘርፍ  አደረጃጀቶች የተደራጁ ሲሆን እነሱም፡-

  1. የወንጀልና የፍትሀብሄር ጉዳዮች ዘርፍ
  2. የህግ ጉዳዮች ዘርፍ
  3. የአስተዳደር እና ፋይናስ ጉዳዮች ዘርፍ ናቸዉ፡፡
  4. የወንጀልና የፍትሀብሄር ጉዳዮች ዘርፍ

ተጠሪነታቸዉ ለወንጀልና ፍትሀብሄር ዘርፍ የሆኑ አምስት ዳይሬክቶረቶች ያሉ ሲሆን እነሱም፤

  1. የሙስና  ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት
  2. የታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት
  3. የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዳይሬክቶረት
  4. የሰቶችና ህጻናት ልዩ የምርመራና ክስ ጉዳዮች ዳይሬክቶረት፤
  5. የፍትሀብሄር ጉዳዮች አስተዳደር ዳይሬክቶረት፤
  6. ህግ ጉዳዮች ዘርፍ ስር የተደራጁ  የስራ ክፍሎች ፡-

ተጠሪነታቸዉ ለህግ ጉዳዮች ዘርፍ የሆኑ ሶስት ዳይሬክቶረቶች ያሉ ሲሆን እነሱም፤

  1. የሕግ ጥናት ፤ ማርቀቅ እና ማስረጽ ዳይሬክቶረት
  2. የጠበቆች፣የሲቪክ ማህበራት እና ሰነድ ምዝገባ ዳይሬክቶረት
  3. ሰብአዊ መብቶች ድርጊት መር ሀግብር እና የትብብር ጥምረት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
  4. የአስተዳደርና ፋይናንስ /ኮርፖረት/ ዘርፍ ስር የተደራጁ  የስራ ክፍሎች

የሚከተሉት የስራ ክፍሎች ተጠሪነታቸዉ ለአስተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ ሆኖ እንዲደራጁ ተደርጓል፡

  1. የሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶረት
  2. ግዥ፣ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  3. ልማት እቅድ ኢኮኖሚ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  4. ኢንፎርሜሼን ኮሚዉንኬሼን ቴክኖሎጂ
  5. ስርዓተ ፆታን በልማት ማካተት
  6. ኤች. አይ. ቪ.ኤይድስ ሜይንስትሪምንግ
  7. ለፍትህ ቢሮ ኃላፊ በቀጥታ ተጠሪ የሆኑ የስራ ክፍሎች
  8. በስራዎቹ ልዩ ባህሪ ወይም በሕግ ለፍትህ ቢሮ ኃላፊ በቀጥታ ተጠሪ እንዲሆኑ የተመለከቱ በመሆናቸዉ ምከንያት አንዳንድ የስራ ክፍሎች ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለፍትህ ቢሮ ኃላፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት፤

  1. የቢሮ ሃላፊ ጽ/ቤት
    1. የህግ ኢንስፔክሽን እና የዜጎች ቅሬታ ማስተናገጃ  ዳይሬክቶረት፤
    1. የመንግስት ኮሙንኬሼን  ዳይሬክቶረት
    1. የውስጥ ኦዲት ዳሬክቶረት
    1. የስነምግባር መከታተያ ክፍል
    1. የዐቃቤ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ፅ/ቤት
    1. ይቅርታ ቦርድ ፅ/ቤት፣
    1. የፍትህ  ሥርዓት ማሻሻያና ፕሮጀክት ጽ/ቤት
  • ተጠሪነታቸዉሰዉ ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶረት የሆኑ የስራ ክፍሎች
    • መረጃ መሰብሰብና ማደራጀት ደጋፊ የስራ ሂደት
    • የሰዉ ሀብት መረጃና  ስታትስትክስ አቅርቦት ደጋፊ የስራ ሂደት
    • የጋራ  አገልግሎት የስራ ክፍሎች ማለትም
  • ጥበቃ አገልግሎት እና የግቢ ውበት ፣
  • የጽዳት አገልግሎት፣