procurement:finance and asset management directorate

የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ፡- የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ የዳይሬክቶሬቱን ሥራዎች ያቅዳል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣ይደግፋል፣በተቋሙ የተመደበ በጀት የፋይናንስ ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ስራ ላይ ያውላል ፣ክፍያ ይፈጽማል፣የተለያዩ የግዢ ውሎችን በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው ጋር ይፈራረማል፣ በተለያዩ ምክንያቶች አገልግልት የማይሰጡ አላቂና ቋሚ ዕቃዎች እንዲለዩ በማድረግ ባለው የመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት ወቅታዊ እርምጃ ይወስዳል፡፡የቋሚ ንብረት መዝገብ በአግባቡ መያዙን ንብረቶች መለያ ቁጥር አግኝተው መመዝገባቸውን ቋሚና አላቂ ንብረቶች በንብረት ሥራ አመራር ደንብና መመሪያዎች መሠረት ገቢና ወጪ መደረጋቸውንና  ለተፈለጉ ዓላማዎች መዋላቸውን ያረጋግጣል፡፡የግዥና ንብረት አስተዳደር ውሳኔዎችን ከመንግሥት ደንብና መመሪያ አንፃር መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡የስራ ክፍሉን ሰራተኞች  የሥራ አፈፃፀም በመገምገም  ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

አቶ ወንድሙ ሳሙኤል አንጁሎ

የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደ ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር