የሴቶችና ህጻናት ልዩ የምርመራና ክስ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክቶሬት
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የሴቶችና ህጻናት ልዩ የምርመራና ክስ ጉዳዮች ክትትል ዳይሬክቶሬት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮን ለማደራጀትና ስልጣንና ተግባሩን ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 12/2016 ላይ ልዩ ድጋፍ ለሚፈልጉ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለሴቶችና ህጻናት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት በተደነገገዉ መሠረት ቀደም ሲል በተቋሙ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ የወንጀል ጥቃቶችና ሌሎች በደሎች ምርመራና ክስ ሥራዎች የተበታተነና አገልግሎቱም በሚፈለገው ልክ ዉጤታማ ባለመሆኑ የስራው ዉጤታማነት በሚፈለገዉ ልክ ባለመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡን ወጥ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን እና ሥርዓት ባለው መልኩ እንዲመራ ለማድረግ አደረጃጀቱ እንደገና ተፈትሾ የመሰረታዊ ስራ ሂደት ጥናት ተጠንቶ የስራ ክፍሉ በቢሮውና በስር መዋቅሮች የተደራጀ የስራ ክፍል ነዉ፡፡
በመሆኑም በስራ ክፍሉ ሴቶችንና ሕጻናትን የሚመለከቱ
- ለሴቶችና ሕጻናት በሕግ ጉዳዮች ላይ የህግ ምክር ድጋፍ መስጠት
- ዕድሜንና ፆታን መሰረት ያደረጉ የወንጀል አቤቱታዎች መመርመር
- በሴቶችና ሕፃናት ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች የወንጀል ክስ የመመስረትና የመከራከር አገልግሎት
- በወንጀል ችሎት መከራከርና ማስወሰን
- ድህረ ወንጀል ዉሳኔ ጉዳዮችን ማለትም የይግባኝ፣የሰበር ጉዳዮች የመካታተልና የቅጣቶች አፈጻጸምን የመከታተል ተግባር
- ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ህጻናት የፍትሐብሔር ክስ መመስረት፣መከራከርና ማስወሰን ይግባኝና ሰበር የመከታተልና የሚወሰኑ ፍርዶችን የማስፈጸም
ተግባራትን የሚያከናዉን ዳይሬክቶሬት ነዉ፡፡ ዳይሬክቶሬቱ ከክልል ማዕከል እስከ ወረዳና ከተማ አስተዳደር ባሉ የፍትህ መዋቅሮች ዐቃብያኔ ህጎችን እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ይዞ የተደራጀ ነዉ፡፡
