የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፡- በዚህ ዳይሪክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ይመለከታል፡-
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!ከሥራ ክፍሎች የሚቀርቡትን የሰው ኃይል ፍላጎት መሰረት በማድረግ የቅጥር፣ የዝውውር እና የደረጃ ዕድገት ጥያቄዎችን ተቀብሎ በተፈለገበት ወቅት እንዲሟላ ያደርጋል፣ የፍትህ ቢሮን የሰው ኃይል ፍላጎት ለማርካት በተፈለገው መጠንና ጥራት የተሟላ /የተመደበ/ የሰው ኃይል መኖሩን ማረጋገጥ፣ መ/ቤቱ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂካዊና ዓመታዊ ዕቅዶችንና ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል በዕውቀታቸው፣ በክህሎታቸውና በአመለካከታቸው የዳበሩ ባለሙያዎችን ያሟላል፤የሠራተኞች የውጤት ተኮር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሞላላቸውና የተሞላላቸውም ውጤት በአግባቡ ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፡፡ የሥራ አፈጻጸም ሥራ አመራር ሥርዓት በመ/ቤቱ እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ የመ/ቤቱን የሥራ ክፍሎች ጋር በመሆን ሠራተኞች በሥልጠና በመደገፍና ክህሎታቸውን በማሳደግ ለሥራ ዝግጁ ያደርጋል፤የመ/ቤቱ ሠራተኞች ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ለሠራተኞች ተስማሚና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር በሥራ አካባቢ የሚኖሩ ችግሮችን በመዳሰስ የመፍትሔ እርምጃ በማቅረብና በማስወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፤በፍትህ ቢሮ በሚሰጠው ምዘና ብቁ ያልሆኑትን ባለሙያዎች ተጨማሪ ስልጠና እንዲያገኙ እና በድጋሚ እንዲመዘኑ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

አቶ ኤርሚያስ ቴማ ቴጋ
የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር
