Director of the legal Audit Inspection and citizens’ complaints directorate

የህግ ኦዲት ኢንስፔክሽንና የዜጎች ቅሬታ ማስተናገጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መልዕክት

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

የህግ ኦዲት ኢንስፔክሽንና የዜጎች ቅሬታ ማስተናገጃ ዳይሬክቶሬት በክልሉ ፍትህ ቢሮ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 12/2016 አንቀጽ 6 (11) የተሰጡትን ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች ስራ ላይ ለማዋል የተደራጀ ዳይሬክቶሬት ሲሆን በስሩም የህግ ኦዲት ቡድን እና የዜጎች ቅሬታ ማስተናገጃ ቡድን የተዋቀረና የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት የሚያከናውን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

  1. በተቋሙ ያሉ ዐቃቤያነ ሕጎች በሕግ መሠረት የሚሰጧቸው ውሳኔዎች ሕግንና አሰራርን ተከትለው የተፈጸሙ ስለመሆኑ በመዝገብ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ማረጋገጥ፤
  2. በሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ስራ የተቋሙን ጠንካራና ደካማ አፈፃፀሞች በመለየት የተቋሙን የመዝገብ ስራ አፈፃፀም በማሳደግ ጥራት ያለው ፍትህ ለዜጎች እንድሰጥ ማገዝ
  3. ተገልጋዮች የሚያቀርቡትን ቅሬታዎች በማጣራት የውሳኔ ሃሳብ ለበላይ አመራር ማቅረብ
  4. በኦዲት ግኝቶች ምርጥ አፈፃፀም  በመነሳት ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋፋት
  5. በቢሮውና በስር መዋቅሮች በዜጎች የአገልግሎት አሰጣጥ ቻርተር እና ስታንዳርድ መሰረት የፍትህ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ማረጋገጥና የዜጎች አገልግሎት እርካታ ዳሰሳ ጥናት ማድረግ
  6. የቢሮው ዐቃቤያነ ሕጎች በሚሰጧቸው ውሳኔዎች የህግና የአሰራር ጥሰቶች በሚፈጸሙበት ጊዜ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የውሳኔ ሀሳብ ለበላይ አመራር በማቅረብ የግልጽነትንና ተጠያቂነትን መርህ ማስፈንና የመሳሰሉትን ተግባራት የሚያከናውን  ሲሆን  ተጠሪነቱም ለቢሮ ኃላፊ ሆኖ የተደራጀ ዳይሬክቶሬት ነው፡፡