Latest regional news

“ምርጫው የዲሞክራሲ መገለጫ በመሆኑ፣ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የፍትህ አካላት የሕግ የበላይነትን የማስከበርና የዜጎችን መብት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው” ብለዋል አቶ ሙሉቀን ታደሰ

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 06/2018 ዓ.ም

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ምርጫ የዲሞክራሲ መገለጫ እንደመሆኑ፣ ይህ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ የፍትህ አካላት የሕግ የበላይነትን የማስከበርና የዜጎችን መብት የማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው” ብለዋል።

ምርጫ የሀገር መንግሥት ግንባታ ምሶሶ ከመሆኑ አንጻር የፍትህ ተቋማት ገለልተኝነት ወሣኝ ጉዳይ ብለዋል።

የወላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት አቶ ምህረት ኩኬ እንዳብራሩት የምርጫ ሥነምግባር ለማስጠበቅ የፍትህ አካላት ገለልተኝነት ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በምርጫ ወቅት ወንጀሎች ስከሰቱ የሰብአዊ መብት በማይጋፋ መንገድ እንዲሆን አሳስበዋል

የምርጫ ወንጀሎች በመለየት ፈጣን ፍትህ እንዲሰጥ ጊዚያዊ ችሎት መዘጋጀቱን አስረድተዋል

ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን የፍትህ ተቋማት ቁርጠኝነት ወሣኝ መሆኑን ገልጸዋል

የጸጥታ አካላት ገለልተኝነት ለምርጫው ውጤታማነት የጎላ ሚና እንደሚጫወት አስረድተዋል

ሠላማዊ ምርጫ ለማካሄድ ቅድሚያ ችግሩን በመለየት በመከላከል ላይ መሠረት በማድረግ ውጤታማነትን ለማስመዝገብ እንደሚሠራ ጠቁመዋል

የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸጋው ስሞኦን እንደገለጹት የጸጥታ አካላት ገለልተኛ እንዲሆንና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ሥልጠናው ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ የተገለጸው።

የምርጫ ቦርዶ አዋጅ መሠረት በማድረግ የጸጥታ አካላት ሕጉን በተከተለ መንገድ ተግበራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

ፍትሕ ተቋማት ምርጫው በሕግ አግባብ እንዲያከናውኑ ሥልጠናው አቅም እንደሚፈጥር አስተያየታቸውን ገልጸዋል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ እና የወላይታ ዞን ፍትህ አካላት በጋር በመሆን ለሥር መዋቅር አካላት ማለትም ለቦዲቲ ከተማ፣ ለዳሞት ጋሌ፣ ለዳሞት ፑላሳ እና ለሻንቶ ከተማ ለተውጣጡ ዐቃቢያነ ሕጎች፣ ዳኞች፣ የፖሊስ አባላት እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ያዘጋጁት የአቅም ግንባታ ስልጠና እና የምክክር መድረክ በቦዲቲ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ እንዲመራ፣ በምርጫ ሕጉ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችንና የወንጀል ተጠያቂነትን በተመለከተ ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ።

‎ላስካ፡ ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

‎የሠላም፣ የሰብዓዊ መብቶችና የዕድገት ማዕከል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር በደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ አስተባባሪነት በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ የመራጮች ትምህርት ስልጠና ከተለያዩ ሲቪል ማህበራት ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ሰጥቷል።

‎ዜጎች በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ስለሚኖራቸው ሚና፣ ኃላፊነቶች እና መብቶች እንዲሁም ለመምረጥ ብቁ ለሆኑ ዜጎች ስለምርጫ ሂደት፣ ሥርዓት፣ መሥፈርቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ የሚፈጥሩ ርዕሶች ላይ ያተኮረ እንደሆነ በስልጠናው ተመልክቷል።

‎የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት መርሆች ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የጠበቆች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሰነድ ማረጋገጫ ዳይሬክተር ዳይሬክቶረት አቶ ደስታ ዮሐንስ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

‎ዜጎች በምርጫ ሂደት ውስጥ በነፃነት የመምረጥና የመመረጥ አጠቃላይ መብቶች እንዲያውቁ፣ እንዲጠቀሙ፤ ምርጫን የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ መሆኑን አቶ ደስታ ዮሐንስ ገልጸዋል።

‎በምርጫ ሂደት ውስጥ ባለድርሻ አካላት የሚኖራቸው ተሣትፎ እና ተግባራቸው እንዲሁም በምርጫ ተዓማኒነት፣ ግልፀኝነት እና የህዝብ ዓመኔታን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው አወንታዊ ተጽዕኖ የላቀ መሆኑን የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ተሰማ ገልፀዋል።

‎መራጮች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም አካላዊ ሁኔታዎችን ጨምሮ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው እንደመሆኑ የምርጫውን ውጤታማነት በማረጋገጥ ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ባለድርሻ መሆናቸውን ተጠቁሟል።

የምርጫ ቦርድ መርሆዎችን በመከተል፣ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ ከወገኝተኝነት በፀዳ መልኩ ባለድርሻ አካላት የዜግነት ኃላፊነትን በተገቢው እንዲወጡ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻ 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የእግር ጉዞ በማድረግ መድረኩ ተጠቃሏል።

‎         ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

‎              ላስካ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፥ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፥ለክልሉ ማረሚያ ኮሚሽን፥ ለዞንና ሬጂኦ ፖሊሲ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች፣ ለምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ለባለድርሻ አካላት በምርጫ ህጎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየሰጠ ነው።

ወላይታ ሶዶ፣ ግንቦት 03/2018 ዓ.ም (ወዞመኮአ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ለዞንና ሬጂኦ ፖሊሲ ከተማ ፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች፣ ለምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ለባለድርሻ አካላት በምርጫ ህጎች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ መስጠት ጀምሯል።

በሥልጠናው የምርጫ አለመግባባት አፈታት ሂደትና የባለድርሻ አካላት ሚና፣ ከምርጫ ጋር የሚያያዙ ወንጀሎች ከምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ከወንጀል ህጉ አንፃር የተዘጋጁ ሰነዶች ይቀርባሉ።

የይቅርታ መስፈርቱን ላሟሉ በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ፡፡

(ሚያዚያ 2/2018፣ሳውላ ፣ ፍትህ ቢሮ)የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ይህን አስመልክተው ማብራርያ የሰጡ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ በክልሉ የይቅርታ አሰጣጥ ህግን መስፈርት በማድረግ በክልሉ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች በ2018 ዓ/ም በሶስተኛ ዙር ይቅርታ እንዲደረግላቸው ከማረሚያ ተቋማት በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የይቅርታ ቦርድ መጋቢት 30/2018 ዓ/ም ባካሄደው  ስብሰባ ተወያይቶ መስፈርቱን ላሟሉ 625 /ለስድስት መቶ ሃያ አምስት/ ታራሚዎች ይቅርታ እንዲደረግላቸው ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል፡፡በዚሁ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደርም የቀረበውን የቦርዱን የውሳኔ ሀሳብ ተቀብለው አፅድቀዋል፡፡

736  ታራሚች በይቅርታ እንዲለቀቁ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ወንድ 593፣ ሴት 32 በድምሩ 625 ታራሚዎች የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው በመገኘታቸው ይቅርታ የተደረገላቸው መሆኑን  ገልጸው፤ ከነዚህ ውስጥ 2(ሁለቱ) የእስራት ተቀናሽ የተደረገላቸው እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ታረሚዎች የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው ባለመገኘታቸው የይቅርታው ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ይቅርታ ከማያሰጡ ምክንያቶች መካከል የተፈጸመው የወንጀል ክብደት፣ለተጎጅ /ቤተሰብ ካሳ አለመክፈል፣ከተጎጅ ቤተሰብ ጋር እርቅ አለመፈጸም የሚሉት እንደሚገኙበት ነው የተናገሩት፡፡

አያይዘውም ከማረሚያ ተቋማት ከግል ተበዳይ እና ከግል ተበዳይ ቤተሰብ ጋር ታራሚዎች ዕርቅ ፈፅመናል በማለት ያቀረቡትን ሰነድ ከክልሉ ማረሚያ ተቋም እና ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በጋራ ማጣራት የተደረገ ስሆን የዕርቅ ሰነድ የቀረበ ቢሆንም የዕርቅ አካል ተደርገው በሰነድ ላይ ፈርመዋል የተባሉት የግል ተበዳይ ሆነ የግል ተበዳይ ቤተሰብ ጥሪ ተደርጎ ባለመቅረባቸው የተነሳ በዕርቅ ሰነድ ላይ የህጋዊነት ጥያቄ በመነሳቱ ምክንያት ውድቅ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም የይቅርታ ተጠቃሚዎች ወደ ህብረተሰቡ በሚቀላቀሉበት ጊዜ በልማት ስራዎች፣በማህበራዊና በልዩ ልዩ መልካም ተግባራት ላይ መሳተፍ፣መተባበር እንደሚኖርባቸው አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል ፡፡

የቢሮ ሀላፊው   በስተመጨረሻ እንኳን ለጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸው ከክርስቶስ የተማርነውን ትህትናና ይቅርታን መሠረት በማድረግ አንዳችን ለአንዳችን አቅም ሁነን በጎነትንና ፍቅርን ከፍ በማድረግ የክርስትናን ስርዓት ለዓለም በማሳየት ሠላምን መስበክ ይኖርብናል ብለዋል። ክርስቶስ ዓለምን በፍቅር  እንዳሸነፈ ሁሉ እኛ ልጆቹም የፍቅርና የሠላም ተምሳሌት መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

በስተመጨረሻም ‎ከክርስቶስ የተማረነውን ፍቅር በመከተል ክርስትናን የሠላም ተምሳሌት በማድረግ ለዓለም እንድናሳይ እያልኩ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን እመኛለሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ከቢሮ ማኔጅመንት አመራር ጋር ገመገመ። 21/07/2018

**************************************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት (9 ወራት) የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን የገመገመ ሲሆን፣ በህግ የተጣለበትን ተልዕኮ በማስፈፀም አስፈላጊ ውጤቶች መመዝገቡን ገልጿል።

ቢሮው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የዜጎች መብት ለመጠበቅ እና የፍትህ አገልግሎትን ተደራሽና ጥራት ያለው ለማድረግ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል። በዚህም የወንጀል ክሶችን በፍ/ቤት መመስረት፣ የሙስናና የታክስ ወንጀሎችን መከታተል፣ የህግ ግንዛቤ መፍጠር እና የህግ ረቂቆችን የማዘጋጀት  ተግባራት እንደተከናወኑ ተገልጿዋል።

በታክስ ማጭበርበር፣ በታክስ ስወራና በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች በግለሰቦች እጅ የገቡትን የመንግስት ሀብት ለማስመለስ እንዲሁም ከቅጣትና ከህገ ወጥ ንግድ ውርስ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ገንዘቦች ገቢ ማስደረግን በተመለከተ በድርድር ብር  ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ተመላሽ መደረጉን ፤

በፍ/ቤት ውሳኔ፣ከወንጀል ቅጣትና ዋስትና ግዴታ ገቢ  ከ3.8 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤

የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም የሚነኩ የፍትሐብሄር ጉዳዮች  ላይ ከክስ በፊት በድርድር  ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን እና ክስ በመመስረት ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት መወሰኑን፤

በፍ/ቤት ክርክርና ክትትል በማድረግ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ መንግስት እንዳይከፍል ለማድረግ መቻሉን፤

በፍትሐብሔር የአፈጻጸም ክስ  ከ142 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤ እንዲሁም

የተመዘበሩ የመንግስት ሀብትና ንብረት ከማስመለስ አንጻር በድርድር  እና በአፈጻጸም ክስ  16.8  ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ  መደረጉ ሪፖርቱ አመለክቷል።

 የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ  ሲያጠቃልል ቢሮው በ9 ወራት ውስጥ ጥሩ አፈፃፀም ማሳየቱን የገለጸ ሲሆን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ። ከእነዚህም ውስጥ በክልል ቢሮ ባለጸደቀ ውል መነሻ ክስ  እንዳይከፈት፤ አዋጪ ያልሆነ መዝገብ ላይ ክስ  መከፈት እንደሌለበት፤ በሀብት ማስመለስ አዋጅ መሠረት አደረጃጀት መፈጠር እንዳለበት፤ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለብን፤ የፌደራል ጉዳዮች መዝገብ አያያዝ ከክልል መዝገቦች በተለየ ሁኔታ መደራጀት እንዳለበት እንዲሁም የ2019 የበጀት ዕቅድ እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት   በፕሮግራም በጀትንግ መሠረት በማዘጋጀት በልማት ዕቅድ በኩል ለክልሉ ፋይናንስ እንዲሁም ፕላን ቢሮ መላክ እንዳለበት  አቅጣጫ በማስቀመጥ በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ክፍተቶችን በመሙላት አፈፃፀሙን ለማሻሻል እንደሚሰራ አስታውቋል።