“የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።” – አቶ ፀጋው ስምዖን
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሴክቶሪያል ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ፣ የካቲት 3/2018 ዓ.ም (ወዞመኮአ)
በጉባኤው ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምዖን የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ መምሪያው አበክሮ እንደሚሠራ አብራርተው የተዘዋዋሪ ችሎት በወር ሁለት ጊዜ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ፀጋው አያይዘውም ከሎጂስቲክስ አቅርቦት ጋር በተያያዘ በታችኞቹ መዋቅሮች እንደሚስተዋል አንስተው ችግሮቹን በመፍታት ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት ተደራሽ እንዲያደርጉ እንደሚሠራም ገልፀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ የህዝብና የመንግሥት ገንዘብ ማስመለስ መቻሉንም ገልጸዋል።
መምሪያው ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት አንዱና ዋንኛው አገልግሎት ማዘመን እንደሆነ የገለጹት አቶ ፀጋው ክስ ከመመስረት ጀምሮ እስከ ፍርድ ሂደት ከእጅ ንክኪ በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለመፈጸም ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
አያይዘውም “ተመር”/TEMER/ ከሚባል የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ጋር ውል በመግባት አገልግሎቱን አውቶሜት የማድረግ ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል።
በወንጀል አስከፊነት ዙሪያ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም እየተሰጡ እንደሆነም አብራርተው በቀጣይ በወጣቱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተናግረዋል።



















