ከብልሹ አሰራርና ከአድሎ የፀዳ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!
ላስካ፡ የካቲት 24/2018 ዓ.ም
የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ 2018 ዓ.ም የመጀመሪያውን ሴክቶሪያል ጉባኤ አካሂዷል።
የፍትህ ተቋማት ትክክለኛና ተገቢነት ያለው ፍትህ ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶክተር ሳሙኤል ደሳለኝ አስገንዝበዋል።
የፍትህ ሥርዓቱን ለማዛባትና ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት አስተዳዳሪው ህግና አሰራርን ያልተከተሉ አሰራሮችን በመለየት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይገባል ስሉ ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም በዞኑ ጠንካራ የፍትህ ሥራዓትን ለመዘርጋት ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዞኑ ከብልሹ አሰራርና ከአድሎ የፀዳ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ተሰማ ተናግረዋል።
ለህብረተሰቡ እየተሰጠ የሚገኘውን የፍትህ አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ሚልክያስ ገልጸዋል።
በመድረኩ የተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና የተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በተቋሙ ልማት ዕቅድ ሥራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ ሳሙኤል አሽኩ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
ከህዝቡ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመፍታት ፍትህን በማረጋገጥና ዘላቂ ልማት ማስፈን እንደሚገባም ተመልክቷል።
በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው መልካም ጅምሮችን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም የተገልጋይ እርካታን ለመጨመር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
ላስካ
