ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ  ነው

March 8, 2026

አዳማ ፤የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የፍትህ ትራንስፎርሜሽን በመተግበር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍትህ ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

በአሁኑ ወቅትም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አተገባበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዘርፉን አሰራር በማዘመን ለውጥ እያመጣ መሆኑ  ይገለጻል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፥መንግስት የማህበረሰቡን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል በፍትህ ተቋማት የሪፎርም ስራ ተግባራዊ ተድርጓል።

ይህንን ተከትሎ በክልሉ ለሙስና የሚያጋልጡ ብልሹ አሰራሮች፣የአቅም ውስንነት፣ የስነ-ምግባር ጉድለት፣የአገልግሎት አሰጣጥና የቅንጅት ችግሮች መፍታት መቻሉን ተናግረዋል።

ለዝርዝሩ፦👉 https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8373028