የኧሌ ዞን ፍትህ መምሪያ ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰትና በሰዉ የመነገድ ተግባር ለመቆጣጠር የፍልሰት ትብብር ጥምረት አቋቁሟል

March 24, 2026

የኧሌ ዞን ፍትህ መምሪያ ህገ-ወጥ የሰዎች ፍልሰትና በሰዉ የመነገድ ተግባር ለመቆጣጠር የፍልሰት ትብብር ጥምረት አቋቁሟል፦

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

#ኮላንጎ:- መጋቢት 10/2018 ዓ/ም #(ኧዞመኮ_AZC)

የኧሌ ዞን ፍትህ መምሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መከላከልና መቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 በማስፈጸሚያ ደንብ 4/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት የፍልሰት ትብብር ጥምረጥ አቋቁሟል፡፡

የኧሌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉድሳ ኩሲያ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ወጣቶች እና ሴቶች ለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተጋላጭና ለስደት ሰለባ ከመሆን መንግስት በሚፈጥረው የስራ ዕድል አማራጭ ሁሉ በመሰማራት በራስ ጥረት የመለወጥ አመለካከትን በማሳደግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀልን ለመከላከል  ግንዛቤ በማያዝ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም በዛሬው እለትም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቅረፍና ዜጎች ለስራ ከሀገር ሀገር ሲንቀሳቀሱ ህጋዊ አሰራሮችን በማስቀመጥ የሚሄዱበትን  ሀገር የሚሰሩትን  ስራ አውቀው ስለሚሄዱበት ሀገርና ስለሚሰሩት  ስራ በቂ ክህሎት ኖሯቸው ይንቀሳቀሱ ዘንድ አጋዥ የሚሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በኧሌ ዞን በሰዉ መነገድና  ሰዉን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ተከላካይ የትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አባይነህ ግርማ  በሰው የመነገድ ወንጀል አንዱ ሕጻናትን ከቦታ ቦታ በህገ-ወጥ መልኩ በማዘዋወር ለጉልበት ብዝበዛ፣ አካላዊና የስነልቦና ጥቃት መፈፀም በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 በስፋት በመቀመጡ ህብረተሰቡ ወንጀልን በመከላከል ሂደት ዉስጥ ያለዉ ድርሻ በቁርጠኝነት ሊወጣ እንደሚገባ  ገልፀዋል፡፡

የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በአዋጁ ላይ ያገኙት ግንዛቤ ህገ ወጥ የሰዎችን ዝውውር ወንጀል ተጋላጭነትን ለመከላከል እና አስፈላጊዉን ጥበቃ ለማድረግ  የሚያስችል በመሆኑ ለህግ አካላት ተገቢዉን ትብብር እንደሚያደርጉ በመጥቀስ፤ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በህይወት ላይ የሚያደርሰውን  አስከፊነት በመረዳት  ወጣቶች በተፈጠረው ህጋዊ አሰራር መሰረት ከዉጪ ሀገራት የስራ ስምምነት በተመቻቸው መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን አጋዥ እንደሚሆኑ በውይይታቸው አስቀምጠዋል።

#መረጃው የኧሌ ዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ነው !!

wpChatIcon
wpChatIcon