የደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ከቢሮ ማኔጅመንት አመራር ጋር ገመገመ። 21/07/2018

April 3, 2026

**************************************

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት (9 ወራት) የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን የገመገመ ሲሆን፣ በህግ የተጣለበትን ተልዕኮ በማስፈፀም አስፈላጊ ውጤቶች መመዝገቡን ገልጿል።

ቢሮው የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣ የዜጎች መብት ለመጠበቅ እና የፍትህ አገልግሎትን ተደራሽና ጥራት ያለው ለማድረግ በርካታ ስራዎችን አከናውኗል። በዚህም የወንጀል ክሶችን በፍ/ቤት መመስረት፣ የሙስናና የታክስ ወንጀሎችን መከታተል፣ የህግ ግንዛቤ መፍጠር እና የህግ ረቂቆችን የማዘጋጀት  ተግባራት እንደተከናወኑ ተገልጿዋል።

በታክስ ማጭበርበር፣ በታክስ ስወራና በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች በግለሰቦች እጅ የገቡትን የመንግስት ሀብት ለማስመለስ እንዲሁም ከቅጣትና ከህገ ወጥ ንግድ ውርስ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ገንዘቦች ገቢ ማስደረግን በተመለከተ በድርድር ብር  ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ ተመላሽ መደረጉን ፤

በፍ/ቤት ውሳኔ፣ከወንጀል ቅጣትና ዋስትና ግዴታ ገቢ  ከ3.8 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤

የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም የሚነኩ የፍትሐብሄር ጉዳዮች  ላይ ከክስ በፊት በድርድር  ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን እና ክስ በመመስረት ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት መወሰኑን፤

በፍ/ቤት ክርክርና ክትትል በማድረግ ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ መንግስት እንዳይከፍል ለማድረግ መቻሉን፤

በፍትሐብሔር የአፈጻጸም ክስ  ከ142 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤ እንዲሁም

የተመዘበሩ የመንግስት ሀብትና ንብረት ከማስመለስ አንጻር በድርድር  እና በአፈጻጸም ክስ  16.8  ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ  መደረጉ ሪፖርቱ አመለክቷል።

 የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ  ሲያጠቃልል ቢሮው በ9 ወራት ውስጥ ጥሩ አፈፃፀም ማሳየቱን የገለጸ ሲሆን በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል ። ከእነዚህም ውስጥ በክልል ቢሮ ባለጸደቀ ውል መነሻ ክስ  እንዳይከፈት፤ አዋጪ ያልሆነ መዝገብ ላይ ክስ  መከፈት እንደሌለበት፤ በሀብት ማስመለስ አዋጅ መሠረት አደረጃጀት መፈጠር እንዳለበት፤ ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለብን፤ የፌደራል ጉዳዮች መዝገብ አያያዝ ከክልል መዝገቦች በተለየ ሁኔታ መደራጀት እንዳለበት እንዲሁም የ2019 የበጀት ዕቅድ እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት   በፕሮግራም በጀትንግ መሠረት በማዘጋጀት በልማት ዕቅድ በኩል ለክልሉ ፋይናንስ እንዲሁም ፕላን ቢሮ መላክ እንዳለበት  አቅጣጫ በማስቀመጥ በቀሪ የበጀት ዓመቱ ጊዜ ውስጥ የተለያዩ ክፍተቶችን በመሙላት አፈፃፀሙን ለማ ሻሻል እንደሚሰራ አስታውቋል።