በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ነዉ

March 13, 2026

መጋቢት 2/2018ዓ/ም(ደኦመኮአ)

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ መምሪያ”ተዓማኒ የፍትህ ስርዓትን ለማረጋገጥ የበኩላችንን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የመምሪያዉ የዕቅድ አፈፃፀም እና የስራ መዋቅር ግምገማ ሴክቶሪያል ጉባኤ መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኦሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደሰ ጋልጶክ የፍትህ ጉዳይ የመምሪያዉና የህግ አካላት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም በለድርሻ አካላት ትኩረት እንደሚያሻ ገልፀዉ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት በማሻሻል ህብረተሰቡ በፍትህ ተቋማት ያለውን እምነት ከፍ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ነፃአለም ኪዳነማሪያም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል አያይዘዉም መምሪያዉ በአዋጅ የተሰጠዉን ተግባርና ኃላፊነት ዉጤታማ ለማድረግ የ7ዓመት ሀገራዊ መሪ ልማት ዕቅድና የ2017 በጀት ዓመት ዉጤት ተኮር እቅድ አፈፃፀም ላይ የታዩ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን መነሻ በማድረግ…

በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ፍትህ እንዲሰፍን፣ የመንግስትና የህዝብ  ጥቅሞች እንዲጠበቁ ፣ በህገመንግስቱ የተደነገጉ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማስቻል የህብረተሰቡ ንቃተ ህሊናን በማሳደግ ረገድ በረካታ ስራዎች እንደተሰሩ ተናግረዋል።

የመምሪያዉ የልማት ዕቅድ ባለሙያ አቶ ሰለሞን ሳጎያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም እያቀረቡ ይገኛል ።

በመድረኩ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ፣የወረዳ አስተዳዳሪዎች እና ከንቲባዎች፣የዞኑ ፖሊስ አዛዥ የሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የፍትህ ጸህፈት ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የመምሪያዉ ማናጅመንት እና የሚመለከታቸው  ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡