የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በትኩረት እየተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ

February 14, 2026

የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በትኩረት እየተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ።

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

29/05/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ)

********************************************

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ በአርባ ምንጭ ከተማ ገምግሟል።

በመድረኩ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋሙ ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት የሚያበረታቱ ውጤቶችን መመዝገቡን ገልፀዋል።

የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲሳኩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ተቋሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆንና ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅሙን በሙሉ በመጠቀም እና አዳዲስ ሀሳቦችን በመተግበር መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

እንዲሁም በየጊዜው የሚሰጡ ተልዕኮዎች በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት በወቅቱ እንዲፈፀሙ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓቶች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አስረድተዋል።

ተግባራት ሲፈጸሙ መርህን መሰረት በማድረግ፣ አውዱን በተገቢው መረዳት እና የዘመኑን ፍላጎት የሚያሟላ ተራማጅ አስተሳሰብ መካከል እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ኃላፊው በተጨማሪም የተቋሙ የፈፃሚ ባለሙያዎች ምዘናና የሪፎርም ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲከናወኑ አሳስበዋል። በዘርፉ የሚስተዋሉ የሰው ኃይል፣ የጥቅማ ጥቅምና ተመሳሳይ ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚፈቱ ገልፀዋል።

በበኩላቸው የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጨርቆስ፣ ተቋሙንና ባለሙያዎችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።

እንዲሁም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማሳካት በተከናወኑ ተግባራት የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና የተስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም እንዳለበት ጠቁመዋል።

የቢሮው ማኔጅመንት አባላትም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በተቋሙ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በመድረኩ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል።