የዜጎችን ሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ውጤታማነት ማረጋገጥ እንዲቻል የባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጂታዊ አሰራርን ማጠናከር ይጠብቃል ተባለ፦ ክቡር አቶ ዱንጋ ናኩዋ።
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት የዕውቅና ሽልማት መርሃግብር መድረክ አካሂደዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ኮሚሽኑ ሀገራችን ከደረሰችበት ሁለንተናዊ የዕድገት ደረጃ የሚመጥንና በሀገራችን እየተካሄደ ከሚገኘው ፈጣን የለውጥ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚጓዝ ዘመናዊ የማረሚያ ፖሊስ ተቋም እንዲሆን በርካታ የለውጥና የሪፎርም ተግባራት እየተከናወነ ይገናኛል ብሏል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በኮሚሽኑ ልማት ዕቅድና በጀት አስተዳደር ክትትልና ግምገማ ግብረመልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተመስገን ያዕቆብ በኩል ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች በይቅርታ አሰጣጥ አፈጻጸም መመሪያ፣ የሞት ፍርደኞች ፣ በአባላት ስነምግባር ጉዳይ እና በሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ አስተያየት ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የፀጥታ ዕቅድ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወንድማገኝ ሰለሞን አቅርቦ ገለፃ ተደርጓል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሉቀን ታደሰ ከቤቱ በተነሱ ጉዳዮች ሰፍ መልስ በመሰጠት በስተመተመጨረሻ የስራ መመሪያ ጭምር በመሰጠት በይቅርታ አሰጣጥ አፈጻጸም መመሪያ፣ በመመሪያው የተካተቱ ጉዳዮች በጥናት ተለይተው እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የክልሉ ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ዱንጋ ናክዋ ሀገሪቱ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው የታራሚዎች አያያዝ ደረጃዎችን ባከበረ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎችን ማስፈጸም በሚያስችል ሁኔታ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት በማክበር እንዲሁም ታራሚዎች ግላዊ ሁኔታ በሚጠይቀው የፍርድ አፈጻጸምና እርምት ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግና ህብረሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም በ8ቱ ተቋማት በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ለታራሚዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የታራሚዎች ደህንነትና ጥበቃ አገልግሎት፣ የቀለም ትምህርትና ሙያ ክህሎት ማሳደግ፣ ምግባር ህክምና አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ በመፈጸም አምራች ዜጋ እንዲሆን ማድረግ ከዋና ዋና ግቦች መሃል የሚጠቀሱ ናቸውም ሲሉ አሳስበዋል።





















