7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና የላቀ እንደሆነ ተገለፀ።

May 26, 2026

‎ላስካ፡ ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

‎የሠላም፣ የሰብዓዊ መብቶችና የዕድገት ማዕከል ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር በደቡብ ክልል ፍትህ ቢሮ አስተባባሪነት በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ የመራጮች ትምህርት ስልጠና ከተለያዩ ሲቪል ማህበራት ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ሰጥቷል።

‎ዜጎች በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ ስለሚኖራቸው ሚና፣ ኃላፊነቶች እና መብቶች እንዲሁም ለመምረጥ ብቁ ለሆኑ ዜጎች ስለምርጫ ሂደት፣ ሥርዓት፣ መሥፈርቶች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ የሚፈጥሩ ርዕሶች ላይ ያተኮረ እንደሆነ በስልጠናው ተመልክቷል።

‎የሥነ-ዜጋና የመራጮች ትምህርት መርሆች ላይ ያተኮረ የስልጠና ሰነድ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የጠበቆች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ሰነድ ማረጋገጫ ዳይሬክተር ዳይሬክቶረት አቶ ደስታ ዮሐንስ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

‎ዜጎች በምርጫ ሂደት ውስጥ በነፃነት የመምረጥና የመመረጥ አጠቃላይ መብቶች እንዲያውቁ፣ እንዲጠቀሙ፤ ምርጫን የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ መሆኑን አቶ ደስታ ዮሐንስ ገልጸዋል።

‎በምርጫ ሂደት ውስጥ ባለድርሻ አካላት የሚኖራቸው ተሣትፎ እና ተግባራቸው እንዲሁም በምርጫ ተዓማኒነት፣ ግልፀኝነት እና የህዝብ ዓመኔታን በማረጋገጥ ረገድ ያላቸው አወንታዊ ተጽዕኖ የላቀ መሆኑን የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ተሰማ ገልፀዋል።

‎መራጮች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም አካላዊ ሁኔታዎችን ጨምሮ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ላይ የተመሰረቱ የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው እንደመሆኑ የምርጫውን ውጤታማነት በማረጋገጥ ረገድ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ባለድርሻ መሆናቸውን ተጠቁሟል።

የምርጫ ቦርድ መርሆዎችን በመከተል፣ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ ከወገኝተኝነት በፀዳ መልኩ ባለድርሻ አካላት የዜግነት ኃላፊነትን በተገቢው እንዲወጡ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻ 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የእግር ጉዞ በማድረግ መድረኩ ተጠቃሏል።

‎         ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም

‎              ላስካ