የፍትህ ቢሮ የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር  ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አምስት ዓመት ትራቴጂክ ዕቅድ ገመገመ

January 23, 2026

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

14/05/2018

******************************

የፍትህ ቢሮ  የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ አምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ  ዕቅድ በሳውላ ከተማ በሚሊነየም አዳራሽ ባካሄደው የሴክተር ጉባዔ የገመገመ ሲሆን በጉባዔ መጀመሪያ ላይ  የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ እንግዶችን እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመክፈቻ ንግገራቸው የፍትህ ሴክተር ጉባዔ የፍትህ ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ሥራዎች፣ ያገኘናቸውን ውጤቶች፣ ያጋጠሙንን ፈተናዎች  እና ወደፊት የምንጓዝበትን አቅጣጫ በግልጽነት ለመገምገም፣ ለመወያየት  እና የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ አስፈላጊ መሠረት ከመጣሉም በላይ በቀጣይ ዘመን የፍትህ አገልግሎታችንን ወደ የተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ይረዳናል  ያሉት ኃላፊው ቢሮው በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በእቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ ሥርዓት እና በመረጃ አስተዳደር ላይ ትኩረት በመስጠት ጉልህ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

የቢሮ ኃላፊውም አክለውም  ቢሮው ባለፉት 6 ወራት ዘላቂ ልማት፣ ሰላም፣ፍትህ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ክልል እውን ለማድረግ ለቀጣይ አምስት ዓመታት (ከ2018 እስከ 2023) የሚዘልቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ  አዘጋጀቷል ያሉት የቢሮ ኃላፊው የስትራቴጂክ ዕቅዱ የለውጥ አመራር ማዕቀፍ በመሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትኩረት መስኮች፣ ግቦችና ውጤቶች በመለየት ፍትህ ቢሮ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ ክብርን መሠረት ያደረገ ማኅበረሰብ ተኮር፣ ተደራሽና ተዓማኒ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት የያዘውን ርዕይ ለማሳካት አቅጣጫ አመላካች ፍኖተ ካርታ ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡

 ከመክፈቻ ንግግር በኃላ  የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸም  በአቶ አብርሃም ለማ እና የስትራቴጅክ ዕቅድ  ሰነድ በአቶ ጤናሁን ጬርቆስ ለጉባዔው የቀረበቡ ሲሆን በታክስ ማጭበርበር፣ በታክስ ስወራና በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች በግለሰቦች እጅ የገቡትን የመንግስት ሀብት ለማስመለስ እንዲሁም ከቅጣትና ከህገ ወጥ ንግድ ውርስ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ገንዘቦች ገቢ ማስደረግን በተመለከተ በድርድር ብር 19,030,508.88 ተመላሽ መደረጉን ፤

በፍ/ቤት ውሳኔ፣ከወንጀል ቅጣትና ዋስትና ግዴታ ገቢ  3,845,860.36 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤

የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም የሚነኩ የፍትሐብሄር ጉዳዮች  ላይ ከክስ በፊት በድርድር  22,680,873.09 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን እና ክስ በመመስረት 32,298,405.28 ብር ለመንግስት መወሰኑን፤

በፍ/ቤት ክርክርና ክትትል በማድረግ ብር 56,557,739.20 መንግስት እንዳይከፍል ለማድረግ መቻሉን፤

በፍትሐብሔር የአፈጻጸም ክስ 125,631,367 ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤ እንዲሁም

የመንግስት ሀብትና ንብረት ገቢ ከማስደረግ አንጻር በድርድር  እና በአፈጻጸም ክስ  148,312,240.09 ብር ለመንግስት ገቢ  መደረጉ፤

በገንዘብ የማይተመኑና በዓይነት ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ የተወሰኑ 949.51 ሄ/ር የገጠር መሬት ፣ 24‚005.92 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ለመንግስት ተመላሽ  እንዲሆን  መደረጉን፤  እንዲሁም  ለ861 ለሚሆኑ  የህግ ታራሚዎች ሙሉ ይቅርታና የእስራት ቅናሽ በክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አማካይነት መደረጉን ዕቅዱ አመላክቷል።

 የቀረቡ ሪፖርትና የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ተከትሎ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በስተመጨረሻም የፍትህ ቢሮ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ  የሚያስችል ዌብሳይት/ድረ ገጽ የማልማትና የተቋሙን ሎጎ  ለጉባዔው ቀርቦ ከጸደቀ በኃላ በይፋ ሥራ እንዲጀምር  ከተደረገ በኃላ የቢሮ ኃላፊው ለቀጣይ የሥራ ጊዜ የሚሆን የሥራ አቅጣጫ ለፍትህ መዋቅር እና ለተጠሪ ተቋም በማስቀመጥ ጉባዔው በስኬት ተጠናቅቋል።