የፍልሰት ትብብር ጥምረት አደረጃጀት በዞኖችና በሪጂዮፖሊስ ከተማ መዋቅሮች እነዲሁም በሥር መዋቅሮች መደራጀት አንዳለበት ተጠቆመ።
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!ጥር 13/05/2018
**** *************************************
በሰው መነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ነማሻገር ወንጀል ለመከላከል በወጣ አዋጅ ቁጥር 1178/2011 መነሻ በተዘጋጀው የፍልሰት ምክር ቤትና ትብብር ጥምረት ደንብ ላይ የምክክር መድረክ የተደረገ ሲሆን የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ መድረኩን ሲያስጀምሩ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የዜጎችን ሰብአዊ ክብር የሚያዋርድና በዜጎች ህይወትና ደህንነት ላይ አሰከፊ አደጋ ከማስከተሉ ባሻገር የሀገርን ክብርና ሎዓላዊነት ጭምር የሚያስደፍር ነው።
በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የፍልሰት ምክር ቤት እና የትብብር ጥምረት ደንብ ቁጥር 94/2017 ለፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የፍትህ ቢሮ ኃላፊው የትብብር ጥምረት አደረጃጀት እስከ ቀበሌ ድረስ የሚዘረጋ ስለሆነ እያንዳንዱ የፍትህ መምሪያ ኃላፊዎች አደረጃጀቱን በሃላፊነት ስሜት ከዞን ጀምሮ በመዘርጋት ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና በሰው የመነገድ ወንጀል የመከላከል ሥራ ከወትሮ እይታችንን በማስፋት እና አሁን ከችግሮች በላይ በመሆን መሥራት አለብን ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ቢሮው ለዞንና ለሪጂዮ ፖሊስ ፍትህ መምሪያ ዐቃቢያነ ህጎች በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 03/2017 ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሰጠ ሲሆን ሥልጠናው የፍትህ ቢሮ ለዞኖች ከሚያደርገው ድጋፍ አንዱ ሲሆን ሥልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል የቢሮ ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጬርቆስ እንዳሉት የፍትህ ዘርፍ ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት በፍትህ ስርዓት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ዓይነትኛ ሚና ያለው እና አንዱ የቅንጅታዊ አሰራር ማሳያ ጭምር ነው ብለዋል።
ምክትል የቢሮ ኃላፊው አክለውም የተሻሻለው የወንጀል የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ዋና ዓላማ የቅጣት አወሳሰን ወጥ፣ ተገማችና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ መሆን እንዳለበትና ወንጀል የፈጸመው አካል ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኝ፣ ቅጣቱ ተቀጪውን እንዲመስል፣ ለተመሳሳይ ጥፋት ተመሳሳይ ቅጣት ጥፋተኛው እንዲያገኝ የሚያደርግ ከመሆኑ በተጨማሪ ህብረተሰቡም በወንጀል ፍትህ ሥርዓት እምነት እንዲኖር እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያስችላል ብለዋል።




















