ከብልሹ አሰራርና ከአድሎ የፀዳ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ
ከብልሹ አሰራርና ከአድሎ የፀዳ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!
ላስካ፡ የካቲት 24/2018 ዓ.ም
የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ 2018 ዓ.ም የመጀመሪያውን ሴክቶሪያል ጉባኤ አካሂዷል።
የፍትህ ተቋማት ትክክለኛና ተገቢነት ያለው ፍትህ ለዜጎች ተደራሽ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶክተር ሳሙኤል ደሳለኝ አስገንዝበዋል።
የፍትህ ሥርዓቱን ለማዛባትና ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት አስተዳዳሪው ህግና አሰራርን ያልተከተሉ አሰራሮችን በመለየት ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ይገባል ስሉ ተናግረዋል።
አስተዳዳሪው አክለውም በዞኑ ጠንካራ የፍትህ ሥራዓትን ለመዘርጋት ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በዞኑ ከብልሹ አሰራርና ከአድሎ የፀዳ የፍትህ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ተሰማ ተናግረዋል።
ለህብረተሰቡ እየተሰጠ የሚገኘውን የፍትህ አገልግሎት ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ሚልክያስ ገልጸዋል።
በመድረኩ የተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ሪፖርትና የተቋሙ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በተቋሙ ልማት ዕቅድ ሥራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ ሳሙኤል አሽኩ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
ከህዝቡ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎችን በመፍታት ፍትህን በማረጋገጥና ዘላቂ ልማት ማስፈን እንደሚገባም ተመልክቷል።
በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በበኩላቸው መልካም ጅምሮችን ለማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም የተገልጋይ እርካታን ለመጨመር እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
ላስካ
የፍትህ ተደራሽነትን በማረጋገጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በላስካ ዙሪያ ወረዳ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል
የፍትህ ተደራሽነትን በማረጋገጥ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በላስካ ዙሪያ ወረዳ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።
ላስካ፦የካቲት 25/2018 ዓ.ም(ዙሪያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን)
⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️ ⚖️
የባስኬቶ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ በአቶ ሚልክያስ ተሰማ የተመራ ልዑክ በዳብፃ ዳልቅንሳ ነፃ የሕግ ድጋፍ ማዕከል በመገኘት የአገልግሎት አሰጣጡንና ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ ተደርጓል።
መምሪያ ኃላፊው አቶ ሚልክያስ ተሰማ የፍትህ ተቋማት ዋነኛ ተልዕኮ ሕዝብን በቅንነትና በቀልጣፋ አሠራር ማገልገል ነው ስሉ ገልፀዋል።
በማዕከሉ ውስጥ የተገልጋዩን ምቾት የሚጠብቁ አሠራሮችን መዘርጋት አገልግሎቱን ለሕዝቡ ቅርብና ግልጽ ማድረግ እንዲሁም በሥራ ሂደት ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን በፍጥነት በመፍታት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
የላስካ ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቤነዘር መሰለ ማዕከሉ የሚጠበቅበትን ሰብአዊና ሙያዊ ግዴታ በብቃት እንዲወጣ ለማድረግ ጽ/ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደማይለየው ገልፀዋል።
አክለው ህብረተሰቡ መብቱንና ግዴታውን ጠንቅቆ እንዲያውቅ የሚያስችሉ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ወንጀል የማይፈጸምባት ሞዴል ቀበሌ ለማድረግ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ የጥበቃና የክትትል ሥርዓት ለመዘርጋት ታልሞ እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
የቀበሌው አመራሮችና ነዋሪዎች የሰላምና የፍትህ ባለቤት በመሆን በቀጣይ የሚጠበቁባቸውን ሥራዎች በቁርጠኝነት ለመወጣት ኃላፊነታቸውን ልወጡ እንደሚገባ ተገልጿል።
የካቲት 25/2018ዓ.ም
ላስካ
ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት











የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መረጃ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ ለክልልና ለሥር መዋቅር ዓቃቢያነ ህግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መረጃ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ ለክልልና ለሥር መዋቅር ዓቃቢያነ ህግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ፣ የካቲት 14/2018 ዓ.ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች መረጃ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ ለክልልና ለሥር መዋቅር ዓቃቢያነ ህግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠት ጀምሯል።
የሥልጠና መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድማገኘሁ አበበ እንደተናገሩት ሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ከማድረስ ባሻገር ሥነልቡናዊም ጉዳት በማድረስ አሉታዊ ተጽእኖአቸው ከፍ ያለ ነው።
በወንጀሎቹ ዙሪያ የመረጃ አሰባሰብ እና ሪፖርት አቀራረብ ላይ የሚሰጠው ሥልጠና ወንጀሉን ለመመርመር መረጃ በመስጠት የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ የተሻለ የፍትህ ውሳኔ ለመስጠት እንደሚያግዝ ተናግረዋል።


















ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው
ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው
አዳማ ፤የካቲት 17/2018 (ኢዜአ)፡-የፍትህ ትራንስፎርሜሽን በመተግበር ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የፍትህ ተቋማትን ሪፎርም በማድረግ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በአሁኑ ወቅትም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አተገባበሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዘርፉን አሰራር በማዘመን ለውጥ እያመጣ መሆኑ ይገለጻል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፥መንግስት የማህበረሰቡን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል በፍትህ ተቋማት የሪፎርም ስራ ተግባራዊ ተድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በክልሉ ለሙስና የሚያጋልጡ ብልሹ አሰራሮች፣የአቅም ውስንነት፣ የስነ-ምግባር ጉድለት፣የአገልግሎት አሰጣጥና የቅንጅት ችግሮች መፍታት መቻሉን ተናግረዋል።
ለዝርዝሩ፦👉 https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8373028


የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ 6ኛ ዙር 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን በታሪካዊ የ130ኛ የአድዋ መታሰቢያ ቀን ላይ አካሄደ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ 6ኛ ዙር 4ኛ መደበኛ ጉባዔውን በታሪካዊ የ130ኛ የአድዋ መታሰቢያ ቀን ላይ አካሄደ።
የካቲት 23/2018 ዓ.ም
******************************************
በጉባዔው መክፈቻ ንግግር ላይ የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባዔ ሰብሳቢና የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ ስለ 130ኛው የአድዋ መታሰቢያ በዓል መልዕክት ሲያስተላልፉ “አድዋ ማለት የማይቻለውን መቻል፣ ዘመናዊ ሥልጠናና የጦር መሣሪያ የታጠቀ ኃይል ማሸነፍ እና የጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ፋና ነው። ዛሬም እንደ ትላንቱ ልዩነቶቻችንን አውርደን ለሀገራችን ክብርና ዕድገት በአንድነት መቆምን ከአድዋ እንማረለን” በማለት ለመላው ኢትዮጵያዊያንና ለጥቁር ህዝቦች መልካም በዓል እንዲሆን ተመኝተዋል።
ከዚህም በመቀጠለ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ 6ኛ ዙር 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ፣ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል። በጉባኤው የተወሰኑ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
- የጥቅማ ጥቅም ረቂቅ መመሪያ መጽደቅ
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ሙሉቀን ታደሰ የቀረበው የዐቃቢያነ ህግ እና የሥራ ኃላፊዎች ጥቅማ ጥቅም ረቂቅ መመሪያ ላይ የጉባኤው አባላት በሰፊው ተወያይተዋል። አባላቱ አስተያየቶችና የውሳኔ ሃሳቦችን ካከሉበት በኋላ መመሪያው የመመሪያ ቁጥር 141/2018 ሆኖ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።
- የጡረታ ዘመን ማራዘሚያ ጥያቄ አንድ ዐቃቤ ህግ የጡረታ ዕድሜያቸው በመድረሱ ምክንያት የሥራ ዘመናቸው እንዲራዘምላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ለጉባኤው ቀርቦ ጉባኤው በቀረበው ጥያቄ ላይ ከመከረ በኋላ በሁለት ዓመት የዐቃቤ ህጉ የጡረታ ዕድሜ እንዲራዘም ወስኗል።
- የደረጃ ምደባ ጥያቄ ቀደም ሲል በዞን መምሪያ ኃላፊነት ተሹመው ሲሰሩ የነበሩና ከሹመታቸው የተነሱ አንድ ዐቃቤ ህግ፣ በክልል ዐቃቤ ህግ ደረጃ ምደባ እንዲሰጣቸው ጥያቄ አቅርበው ጉባኤው ጥያቄውን በዐቃቢያነ ህግ የቅጥር፣ ምደባ እና የዝውውር አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 80/2017 አንቀጽ 19(1) መሠረት በመመርመር ውድቅ እንዲሆን ወስኗል።
በመጨረሻም ዋና ጉባኤው ፦
* ዐቃቢያነ ህግ ጉዳዮቹ እስኪፈጸሙ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ፤
* ከሙያዊ ሥነ-ምግባር ውጪ በሆኑ መንገድ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሚሰራጩ አሉባልታዎች እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስቧል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ















የዜጎችን ሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ውጤታማነት ማረጋገጥ እንዲቻል የባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጂታዊ አሰራርን ማጠናከር ይጠብቃል ተባለ፦ ክቡር አቶ ዱንጋ ናኩዋ
የዜጎችን ሰብዓዊ መብት አጠባበቅ ውጤታማነት ማረጋገጥ እንዲቻል የባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጂታዊ አሰራርን ማጠናከር ይጠብቃል ተባለ፦ ክቡር አቶ ዱንጋ ናኩዋ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት የዕውቅና ሽልማት መርሃግብር መድረክ አካሂደዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ኮሚሽኑ ሀገራችን ከደረሰችበት ሁለንተናዊ የዕድገት ደረጃ የሚመጥንና በሀገራችን እየተካሄደ ከሚገኘው ፈጣን የለውጥ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚጓዝ ዘመናዊ የማረሚያ ፖሊስ ተቋም እንዲሆን በርካታ የለውጥና የሪፎርም ተግባራት እየተከናወነ ይገናኛል ብሏል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በኮሚሽኑ ልማት ዕቅድና በጀት አስተዳደር ክትትልና ግምገማ ግብረመልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ተመስገን ያዕቆብ በኩል ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች በይቅርታ አሰጣጥ አፈጻጸም መመሪያ፣ የሞት ፍርደኞች ፣ በአባላት ስነምግባር ጉዳይ እና በሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ አስተያየት ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የፀጥታ ዕቅድ በኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ወንድማገኝ ሰለሞን አቅርቦ ገለፃ ተደርጓል።
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሉቀን ታደሰ ከቤቱ በተነሱ ጉዳዮች ሰፍ መልስ በመሰጠት በስተመተመጨረሻ የስራ መመሪያ ጭምር በመሰጠት በይቅርታ አሰጣጥ አፈጻጸም መመሪያ፣ በመመሪያው የተካተቱ ጉዳዮች በጥናት ተለይተው እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የክልሉ ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ዱንጋ ናክዋ ሀገሪቱ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባላቸው የታራሚዎች አያያዝ ደረጃዎችን ባከበረ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡ ውሳኔዎችን ማስፈጸም በሚያስችል ሁኔታ የታራሚዎችን ሰብዓዊ መብት በማክበር እንዲሁም ታራሚዎች ግላዊ ሁኔታ በሚጠይቀው የፍርድ አፈጻጸምና እርምት ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግና ህብረሰቡ ጋር የሚቀላቀሉበት ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም በ8ቱ ተቋማት በፍርድ አፈጻጸም ሂደት ለታራሚዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የታራሚዎች ደህንነትና ጥበቃ አገልግሎት፣ የቀለም ትምህርትና ሙያ ክህሎት ማሳደግ፣ ምግባር ህክምና አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ በመፈጸም አምራች ዜጋ እንዲሆን ማድረግ ከዋና ዋና ግቦች መሃል የሚጠቀሱ ናቸውም ሲሉ አሳስበዋል።





















የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህ ቢሮ የስድስት ወር የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በአርባምንጭ ከተማ ገመገመ
የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህ ቢሮ የስድስት ወር የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም በአርባምንጭ ከተማ ገመገመ።
07/06/2018 ዓ.ም (አርባምንጭ)
**************************************,
በፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ሕግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በሆኑት አቶ በላይሁን ይርጋ የተመራ የፌዴራል ልዑክ ቡድን በአርባምንጭ ከተማ በክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ፣ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ፣ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዱንጋ ናኩዋ እና የምክር ቤቱ የሕግ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ መስከረም ደገፉ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህ ቢሮ የስድስት ወራት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
የተቋሙን የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የሰባዓዊ መብቶች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊና የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ፎካል ፐርሰን አቶ ታይሰን ማጆሬ ሲሆኑ፣ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ተግባራት የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መፈፀማቸውንና አስተዋጽኦአቸውም ከፍተኛ መሆኑን በሪፖርቱ ገልፀዋል።
በሀገር ደረጃ በልዩ ትኩረት የተጀመረውን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ሥራ በክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ለማስፈፀም፣ ዜጎች ከፍትህ ተቋማት የሚያገኙትን አገልግሎት ፍትሃዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ሥራዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል።
ልዑኩ የተከናወኑ ሥራዎችን፣ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና ቀጣይ ሊሰሩ የሚገቡ ጉዳዮችን ከገምገመ በኋላ፣ የሚከተሉትን እንደ ጠንካራ ጎኖች አመልክቷል፦
- የባህል ፍርድ ቤቶች አዋጅ መዘጋጀቱ፣
- የአስተዳደር ሥነ ሥርዓት አዋጅ መጽደቁና የመመሪያ ዝግጅት መጀመሩ፣
- የክልሉ የፍልሰት ምክር ቤትና የትብብር ጥምረት ደንብ መዘጋጀቱና ወደ ተግባር መግባቱ፣
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥራዎችን ለማሳካትና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ ዌብሳይት መበልጸጉ፣
- የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ግብረ ኃይል (Task Force) መቋቋሙ፣
- ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሕግ ግንዛቤ መሰጠቱ።
በሌላ በኩል የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ከፖሊስ ጋር በመፈራረም ተግባራዊ አፈጻጸሙን ማጠናከር፣ ለባህላዊ ዳኝነት የተመረጡ ሽማግሌዎችን ማሰልጠን፣ ለትራንስፎርሜሽን ሥራዎች በቂ በጀት መመደብ እና በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተጠቅሰዋል።
በመጨረሻም፣ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ሥራዎችን በቀጣይ ጊዜ ይበልጥ በቅንጅትና በውጤታማነት ለማስፈፀም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠው፣ ውይይቱ ተጠናቋል።













የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በትኩረት እየተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ
የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በትኩረት እየተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ።
29/05/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ)
********************************************
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ያሉበትን የአፈፃፀም ደረጃ በአርባ ምንጭ ከተማ ገምግሟል።
በመድረኩ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋሙ ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት የሚያበረታቱ ውጤቶችን መመዝገቡን ገልፀዋል።
የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲሳኩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ተቋሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆንና ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅሙን በሙሉ በመጠቀም እና አዳዲስ ሀሳቦችን በመተግበር መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።
እንዲሁም በየጊዜው የሚሰጡ ተልዕኮዎች በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሠረት በወቅቱ እንዲፈፀሙ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓቶች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አስረድተዋል።
ተግባራት ሲፈጸሙ መርህን መሰረት በማድረግ፣ አውዱን በተገቢው መረዳት እና የዘመኑን ፍላጎት የሚያሟላ ተራማጅ አስተሳሰብ መካከል እንዲሆኑ አሳስበዋል።
ኃላፊው በተጨማሪም የተቋሙ የፈፃሚ ባለሙያዎች ምዘናና የሪፎርም ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲከናወኑ አሳስበዋል። በዘርፉ የሚስተዋሉ የሰው ኃይል፣ የጥቅማ ጥቅምና ተመሳሳይ ችግሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚፈቱ ገልፀዋል።
በበኩላቸው የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጤናሁን ጨርቆስ፣ ተቋሙንና ባለሙያዎችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
እንዲሁም የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ስራዎችን ለማሳካት በተከናወኑ ተግባራት የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና የተስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም እንዳለበት ጠቁመዋል።
የቢሮው ማኔጅመንት አባላትም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት በተቋሙ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።













የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ተግባር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር ተግባር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።
ሣውላ፦ጥር 27/2018 ዓ/ም
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ መንፈቀ ዓመት 6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ከሥር መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማና የቀጣይ ሥራዎች የትኩረት አቅጣጫ የማስቀመጥ መድረክ አካሂዷል።
የጎፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደመላሽ ብላቴ እንደተናገሩት መምሪያው የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት የ5 ዓመት መሪ ዕቅዶችን ከልሶ ተግባራትን እየሰራ ይገኛል በማለት ገልፀዋል።
መሪ ዕቅድን መነሻ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊመብቶችን ለማክበርና ለማስከበር እንዲሁም መብትና ግዴታውን ጠንቅቆ የሚያቅ ህብረተሰብ ለመፍጠር በሁሉም አካባቢ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በመቀጠልም በዋና ዋና ዘርፎች በልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዩች ፤የሴቶችና ህፃናት ልዩ ምርመራ ክስ ጉዳዮች ታክስና ኢኮኖሚ ወንጀሎች የሙስና ወንጀል ጉዳዮች መንግስት የከሰሰባቸው የፍትሃብሄር ጉዳዮችን ለይቶ በጥብቅ ድስፕሊን በመሰራቱ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
በመደበኛ ፍርድ ቤት የተደረጉ የቀጥታ መደበኛ ክስ ክርክር ክትትል የሚቀርቡ ክሶችን በመመርመር ቀልጣፋና አፋጣኝ ውሳኔዎችን በመስጠት አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በፍትሐብሄር ጉዳዮች መንግስት ክሶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት 7,294,384 ብር በማስመለስ ውጤታማ ስራ መስራቱን ተናግሯል።
በፍትሐብሄር ጉዳዮች መንግስት የተከሰሰባቸውን ጉዳዮች ላይ በዐቃቤ ህግ መሰረት በመካሰስ ተገቢውን ክርክር በማድረግ መመለስ ያለበትን በመመለስ መንግስት መክፈል የሚገባውን እንዲከፍል ተደርጓል ብለዋል።
በተጨማሪም በአንዳንድ አካባቢዎች እጅግ ጫፍ የወጡ የመሬት ወረራዎችን በተመለከተ በጣም ፈታኝና የመሬት አስተዳደርን መሰረት አድርጎ አሰጣጡም ሆነ አወሳሰዱም ህጋዊ እንዲሆኑ ከግንዛቤ መፍጠር ጀምሮ መሬትን የማስመለስ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ተወካይና አቶ ለማላ አብርሃም በየፍርድ ቤቱ በመንግስት በኩል የሚከሰሱ ክሶችን በተገቢው መንገድ ውሳኔ እንዲያገኙ ዐቃቤያነ ህጎች በመረጃና በማስረጃ ግልፅ አቀራረብ በመጠቀም ማስፈፀም ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በፍትህ ስርዓቱ ላይ መፈታትና በቁርጠኝነት ሊሰሩ የሚገቡ በተለይ ተከሳሽ በጊዜ የማቅረብና የተሳለጠ ቀልጣፋ ስራ እንዲሰራ የማድረግ ስራን በይበልጥ መስራት ያስፈልጋል በማለት ተናግረዋል።
በመጨረሻም የተግባር አፈፃፀም ሰነድ ቀርቦ የጋራ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊ አካላት ሃሳብ አስተያዬት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል
“የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ እና የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።” – አቶ ፀጋው ስምዖን
የወላይታ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሴክቶሪያል ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ፣ የካቲት 3/2018 ዓ.ም (ወዞመኮአ)
በጉባኤው ላይ አግኝተን ያነጋገርናቸው የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምዖን የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥ መምሪያው አበክሮ እንደሚሠራ አብራርተው የተዘዋዋሪ ችሎት በወር ሁለት ጊዜ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አቶ ፀጋው አያይዘውም ከሎጂስቲክስ አቅርቦት ጋር በተያያዘ በታችኞቹ መዋቅሮች እንደሚስተዋል አንስተው ችግሮቹን በመፍታት ወረዳ እና ከተማ አስተዳደሮች የተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት ተደራሽ እንዲያደርጉ እንደሚሠራም ገልፀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የተመዘበረ የህዝብና የመንግሥት ገንዘብ ማስመለስ መቻሉንም ገልጸዋል።
መምሪያው ትኩረት ከሚሰጣቸው ተግባራት አንዱና ዋንኛው አገልግሎት ማዘመን እንደሆነ የገለጹት አቶ ፀጋው ክስ ከመመስረት ጀምሮ እስከ ፍርድ ሂደት ከእጅ ንክኪ በፀዳ መልኩ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ለመፈጸም ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
አያይዘውም “ተመር”/TEMER/ ከሚባል የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ጋር ውል በመግባት አገልግሎቱን አውቶሜት የማድረግ ሥራ መጀመሩንም ጠቁመዋል።
በወንጀል አስከፊነት ዙሪያ የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም እየተሰጡ እንደሆነም አብራርተው በቀጣይ በወጣቱ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ተናግረዋል።
ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም አደመጠ
ሀዋሳ: ጥር 29/2018 ዓ.ም (ደሬቴድ) ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም ገምግሟል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ 6 ወራት ሥራ አፈፃፀም በዝርዝር ተመልክቷል።
የተቋሙን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርቡት የፍትህ ቢሮ ምክትል ሀላፊና የወንጀልና ፍትሃብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጤናው ጨርቆስ፥ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልዋል::
የሙስና እና የታክስ ወንጀሎች በፍርድ ቤት ክስ በመመሠረት አሰተማሪ ቅጣት እንዲያገኙ በትኩረት መሠራቱን የገለፁት ኃላፊው፥ የፍትህን የማረጋገጥ ስራዎች የህብረተሰቡ ተሳትፎ በማጠናከር እና በየአካባቢው ያሉ የፀጥታ ስጋቶችን ለይቶ በመፍታት የክልሉን አንጻራዊ ሰላም ማፅናትና አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ጠንካራ እና አስተማማኝ ተቋም በመገንባት የፍትህ ስርዓቱን በማጠናከርና አስተማማኝ ደረጃ ከማድረስ ባለፈ፥ በተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ገልፀዋል።
ቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ግልፅነትና ማብራሪያ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ጥያቄና አስተያየት ሰጥተዋል::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደሰ ቋሚ ኮሚቴዉ ላቀረበው ጥያቄና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ የመንግስትና የህዝብ ሃብት ያለባቸዉ የፍትሃብሔር ወንጀሎች የተሻለ አፈፃ ፀም መመዝገቡን ገልፀዋል::
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቶ ዱንጋ ናኩዋ፣ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ታራሚ ይቅርታ አሰጣጥ ግልኝንነት፣ ከማረም ማነጽ በተያያዘ በፍትህ ተቋማት የሚሰተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ በጋራ መሥራት ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ: ተስፋዬ ወ/ማሪያም
የፍትህ ቢሮ የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አምስት ዓመት ትራቴጂክ ዕቅድ ገመገመ
የፍትህ ቢሮ የ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አምስት ዓመት ትራቴጂክ ዕቅድ ገመገመ፤
14/05/2018
******************************
የፍትህ ቢሮ የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ አምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ በሳውላ ከተማ በሚሊነየም አዳራሽ ባካሄደው የሴክተር ጉባዔ የገመገመ ሲሆን በጉባዔ መጀመሪያ ላይ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ እንግዶችን እንኳን በደህና መጣችሁ ካሉ በኃላ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመክፈቻ ንግገራቸው የፍትህ ሴክተር ጉባዔ የፍትህ ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸውን ሥራዎች፣ ያገኘናቸውን ውጤቶች፣ ያጋጠሙንን ፈተናዎች እና ወደፊት የምንጓዝበትን አቅጣጫ በግልጽነት ለመገምገም፣ ለመወያየት እና የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ አስፈላጊ መሠረት ከመጣሉም በላይ በቀጣይ ዘመን የፍትህ አገልግሎታችንን ወደ የተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ይረዳናል ያሉት ኃላፊው ቢሮው በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በእቅድ ዝግጅት፣ በክትትልና ግምገማ ሥርዓት እና በመረጃ አስተዳደር ላይ ትኩረት በመስጠት ጉልህ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊውም አክለውም ቢሮው ባለፉት 6 ወራት ዘላቂ ልማት፣ ሰላም፣ፍትህ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ክልል እውን ለማድረግ ለቀጣይ አምስት ዓመታት (ከ2018 እስከ 2023) የሚዘልቅ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ አዘጋጀቷል ያሉት የቢሮ ኃላፊው የስትራቴጂክ ዕቅዱ የለውጥ አመራር ማዕቀፍ በመሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የትኩረት መስኮች፣ ግቦችና ውጤቶች በመለየት ፍትህ ቢሮ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ ክብርን መሠረት ያደረገ ማኅበረሰብ ተኮር፣ ተደራሽና ተዓማኒ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት የያዘውን ርዕይ ለማሳካት አቅጣጫ አመላካች ፍኖተ ካርታ ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል፡፡
ከመክፈቻ ንግግር በኃላ የስድስት ወር የዕቅድ አፈጻጸም በአቶ አብርሃም ለማ እና የስትራቴጅክ ዕቅድ ሰነድ በአቶ ጤናሁን ጬርቆስ ለጉባዔው የቀረበቡ ሲሆን በታክስ ማጭበርበር፣ በታክስ ስወራና በተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች በግለሰቦች እጅ የገቡትን የመንግስት ሀብት ለማስመለስ እንዲሁም ከቅጣትና ከህገ ወጥ ንግድ ውርስ ገቢ ሊሆኑ የሚገባቸውን ገንዘቦች ገቢ ማስደረግን በተመለከተ በድርድር ብር 19,030,508.88 ተመላሽ መደረጉን ፤
በፍ/ቤት ውሳኔ፣ከወንጀል ቅጣትና ዋስትና ግዴታ ገቢ 3,845,860.36 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤
የመንግስትና የሕዝብ ጥቅም የሚነኩ የፍትሐብሄር ጉዳዮች ላይ ከክስ በፊት በድርድር 22,680,873.09 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉን እና ክስ በመመስረት 32,298,405.28 ብር ለመንግስት መወሰኑን፤
በፍ/ቤት ክርክርና ክትትል በማድረግ ብር 56,557,739.20 መንግስት እንዳይከፍል ለማድረግ መቻሉን፤
በፍትሐብሔር የአፈጻጸም ክስ 125,631,367 ለመንግስት ገቢ መደረጉን፤ እንዲሁም
የመንግስት ሀብትና ንብረት ገቢ ከማስደረግ አንጻር በድርድር እና በአፈጻጸም ክስ 148,312,240.09 ብር ለመንግስት ገቢ መደረጉ፤
በገንዘብ የማይተመኑና በዓይነት ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ የተወሰኑ 949.51 ሄ/ር የገጠር መሬት ፣ 24‚005.92 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆን መደረጉን፤ እንዲሁም ለ861 ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ሙሉ ይቅርታና የእስራት ቅናሽ በክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አማካይነት መደረጉን ዕቅዱ አመላክቷል።
የቀረቡ ሪፖርትና የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ ተከትሎ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በስተመጨረሻም የፍትህ ቢሮ ሥራዎችን ለማቀላጠፍ የሚያስችል ዌብሳይት/ድረ ገጽ የማልማትና የተቋሙን ሎጎ ለጉባዔው ቀርቦ ከጸደቀ በኃላ በይፋ ሥራ እንዲጀምር ከተደረገ በኃላ የቢሮ ኃላፊው ለቀጣይ የሥራ ጊዜ የሚሆን የሥራ አቅጣጫ ለፍትህ መዋቅር እና ለተጠሪ ተቋም በማስቀመጥ ጉባዔው በስኬት ተጠናቅቋል።
በጉባኤው የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕረዝዳንት ክቡር አቶ ቦጋለ ፈይሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የዞንና የሪጂዮ ፖሊስ ከተሞች የመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የሴቶችንና የህፃናትን ጥቃት የማይታገስ ማህበረሰብ መፈጠር እንዳለበት ተጠቆመ
30/03/2018
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች “ጥቃትን የማየታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በዓለም ለ34ኛ፣በሀገራችን ለ20ኛ እንዲሁም በክልላችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን የነጭ ሪቫን ቀን አክብረዋል።
የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ የሴቶች ጥቃት የሁላችንም ጥቃት በመሆኑ ሁላችንም ጥቃቱን ለመከላከል ከራሳችን ቤት እና ጓዳ መጀመር አለብን ሲሉ በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን የፍትህ ቢሮ የሕግ ማርቀቅ፣ ማስረጽ እና ግንዛቤ መፍጠር ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀሐይነሽ አበራ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መንስዔዎችን፣ የጥቃት ምንነትና ትርጉም፣ጥቃት የሚያደርሰውን አካላዊ፣ሥነ ልቦናዊ እንዲሁም የሚያስከትለውን ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚያመላክትና በቀጣይ መደረግ ያለበትን የትኩረት አቅጣጫ አመላካች ሰነድ አቅርባለች።
በቀረበው ሰነድ ላይ ለተነሳው አስተያየትና ጥያቄ ምክትል የቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ወንድማገኘሁ አበበ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የሴቶችና ህፃናት ጥቃት በእኔ እናት፣ በእኔ ልጅ ፣ በእኔ ሚስት እንዲሁም በሀገሬ ላይ የሚፈፀም ጥቃት ነው ብለን ማሰብ አለብን ሲሉ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን አክለውም ዛሬ በአንዲት ሴት እና ህጻን ላይ የተፈጸመ ጥቃት ተራው ደርሶ ነገ በእኔ ቤት ባሉ ሴቶችና ህጻናት ላይ እንደሚፈጸምና አልፎ ተርፎም በአጠቃላይ በማህረስብ ጭምር ላይ ሊፈፀም እንደሚችል ያስገነዘቡት ምክትል የቢሮ ኃላፊው ከጥቃት የተነሳ ይህቺ ዓለም ለሴቶችና ህጻናት ‘ገሃነም ሆኗለች’ ያሉ ሲሆን ጥቃትን ለመከላከል ማህበረሰብን ማነቃነቅና ሞብላይዝ ማድረግ፤ አስቀድሞ ጥቃቱን የመከላከል ስትራተጂ መንደፍ፤ ጥቃት አድራሾችን ከማህበረሰቡና ከሥራ ማግለል እንዲሁም ተገቢውንና የወንጀሉን ሕጉን የተከተለ ቅጣት መቅጠትና ጥቃት ከደረሰ በኃላ የሚመጡት ተበዳዮች ሁለተኛ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ተገቢውንና ቀልጣፋ ፍትህ ማግኘት አለባቸው ሲሉ የመፍትሔ አቅጣጫ ያሏቸውን የጠቆሙ ሲሆን፦
በስተመጨረሻም የፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ታደሰ ሲያጠቃልሉ የነጭ ሪቫን ቀን ስናከብር መርሃ ግብር ብቻ ለማሟላት እና በዚህ መድረክ ላይ አውርተን ነገ ለመርሳት ሳይሆን በተግባር ከቤታችን ጀምረን በሰራተኞቻችን ላይ ከምንፈጽመው ከጉልበት ብዝበዛ ጭምር መቆጠብ እንዳለብንና ከውጭ ያለውን ጥቃት መታገል እንዳለብን ያነሱ ሲሆን አክለውም በክልሉ ውስጥ የሴቶችና ህፃናት ጥቃት በየዓመቱ እየጨመረ ነው ወይንስ እየቀነሰ ነው የሚለውን ለማወቅ ጥናት ተደርጎ በቀጣይ ሰነድ ተዘጋጅቶ ጥናታዊ ጽሑፍ መቅረብ እንዳለበት አቅጣጫ በማስመቀጥ መርሃ ግብሩ ተጠናቅቋል ።
ሀሹ ሀሹ ቶጵያ ዴሪያሲ፤ ሀሹ ሀሹ ቶሆሳ ቶጵያ ደሪያሲ፤ ሀሹ ሀሹ ዎላይታ ደሪያሲ!!





































































