office of the chief prosecutor’s office

የዐቃቢያነ ሕግ አስተዳደ ዋና ጉባኤ ጽህፈት ቤት መልዕክት

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮን ለማደራጀትና ስልጣንና ተግባሩን ለመወሰን በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 12/2016 አንቀጽ 13 መሠረት የተቋቋመ ሲሆን በጽ/ቤቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ፡-

ከዐቃቤ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጋር በመሆን  የዐቃቢያነ ሕግ ሹመት፣ቅጥር፣ ምደባ፣ ዝውውር፣ የዕረፍት ጊዜ፣ የአገልግልት ዘመን፣ ደረጃ፣ ሥነ-ምግባር፣ አደረጃጀት፣ መዋቅር፣ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና የመሳሰሉ ጉዳዩችን ያካተተ የተለያዩ መመሪያዎች ግብአት የማሰባሰብ ስራ ይሰራል፣ ረቂቆችን ያዘጋጃል፤ለሚመለከተዉ አካል አቅርቦ በማፀደቅ ስራ ላይ እንዲዉል  ክትትል ያደርጋል፣ የዐቃቢያነ ሕግ ስምሪትና የአሰራር ዉጤታማነት ማሻሻያ ስርዓት ይቀርፃል ይተገብራል፣ የዐቃቢያነ ሕግ የስራ የምዘና ሥርዓት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን ይቀርፃል፣ በየወቅቱ እንደመዘኑ ይከታተላል፣ በዐቃቢያነ ሕግ የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አበቱታዎችን በማጣራት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር የመፍትሔ አቅጣጫ እንዲቀመጥ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤  በዐቃቢያነ-ህግ ላይ ሚቀርቡ የዲስፒሊን እርምጃ አወሳሰድ ህግንና ሥነ-ሥርዓትን የተከተለ መሆኑን ይከታተላል፣

ለዐቃቢያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤው የሴክሬታሪያት አገልግሎት ይሰጣል፣ በጉባኤው የተወሰኑ ውሳኔዎችን እና ቃለ-ጉባኤዎችን አደራጅቶ ይይዘል፣ በዋና ጉባኤ እና በቢሮ ኃላፊ የፀደቁትን ውሳኔዎችን አፈፃፀም ይከታተላል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አዲስ ለሚቀጠሩ ዐቃብያነ ሕግ የስራ የማስተዋወቂያ ስልጠና (Inducation) እንዲሁም ተግባር ተኮርና ሙያ ብቃት ማረጋጫ የቅድመ ስራ ስልጠና እንዲወስዱ ያደርጋል፣ የዐቃቤያን ሕግ ደህንነትና ጤንነት እንዲጠበቅ ለሠራተኞች ተስማሚና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር በሥራ አካባቢ የሚኖሩ ችግሮችን በመዳሰስ የመፍትሔ እርምጃ በማቅረብና በማስወሰን ተግባራዊ ያደርጋል፤የጉባኤው ውሳኔ በማይጠይቁ የዐቃቤያን ሕግ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፣  በዐቃቢያነ ሕግ ዋና ጉበኤ እና በቢሮ ኃላፊ የሚሰጡትን ለሎች ተግባራትን ያከናዉናል፡፡