directorate of development planning and economic management

የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

በዚህ የስራ ሂደት የዕቅድ ዝግጅት፣ የእቅድ አፈፃፀም ክትትልና ግምገም፣  የሪፖርት ዝግጅትና ግብረ መልስ፣ የፕሮጀክት ጥናት ክትትልና ግምገማ፣የበጀት ዝግጅትና ክትትል የሚመለከቱ ጉዳዮችን ያከናውናል፡፡ይህም ማለት፡-

የተቋሙን  የፊዚካልና የበጀት ዕቅድ ያቅዳል፣ወቅቱን ጠብቆ ተቋማዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤የዘረፉ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ወቅቱን ጠብቆ  በየ ሩብ ዓመቱ፣የመንፈቅና ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም በማዘጋጀት እንዲገመገም ያደርጋል፡፡በተቋሙ ውስጥ የሚካሄደው የለውጥ እንቅስቃሴ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ውጤታማ እንዲሆን ያስተባብራል ይከታተላል፡፡

በተጨማሪም የሴክተሩ የፍትህ ፖሊሲ መነሻ ያደረገና አቅምን ያገናዘበ ሁሉ አቀፍና የተቀናጀ የረጅም፣የመካከለኛ እና የአጭር ጊዜ መሪ የልማት እቅድ /ፕሮግራም ማዘጋጀትና የዕቅድ ዝግጅት ሂደቱን ወቅታዊ ፣ አሳታፊና ቀጣይነት ያለው ፍትህን ሊያሰፍንና መልካም አስተዳደርን ሊያመጣ የሚችል እንዲሆን ይደረጋል፡፡

የክትትልና ግምገማ አሰራር ከተቋሙ አስተዳደር ስርዓት ጋር የተጣጣመ ፣ተከታታይ ፣ወቅታዊ፣አሳታፊ፣በጥረት የሚከናወንና ግብረ-መልስ የሚሰጥበት እንዲሆን ይደረጋል፡፡ዕቅድና በጀት የበጀት ዓመት ከማለቁ በፊት ተዘጋጅቶና ፀድቆ ለሥራ ሂደቶች እንዲደርስ ይደረጋል፡፡የሚመለከታቸውን በማሳተፍ የተዘጋጁና የፀደቁ የልማት ዕቅድ የግማሽ ዘመን አፈፃፀም ግምገማ/ Midterm Review/ እና የመጨረሻ ዘመን አፈፃጸም ግምገማ /Terminal Evaluation/ ሪፖርቶች ያዘጋጃል፡፡

ከፋ/ኢ/ል/ቢሮ በተዘጋጀ መመሪያ መሠረት ማኑዋል በስራ ላይ ያውላል፣

ወ/ሮ መሠከረም ሁሴን ይማም

የልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ግብረ መልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር