የፍትሐብሔር ጉዳዮች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!ዳይሬክቶሬቱ የሕዝብ እና የክልል መንግስት መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከሳል፣ መልስ ይሰጣል፣ ይከራከራል፤ ይደራደራል፣ ዉሳኔ ይሰጣል/ያሰጣል፣ በሕግ መሠረት ውሳኔዎችን ያስፈፅማል ፡፡ የፍትሐብሔር ክስ ለመመሥረት የገንዘብ አቅም የለላቸውን ዜጎች በተለይም ሴቶችን፣ ሕፃናትን፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋውያንን ወክሎ ይከራከራል፡፡ አለአግባብ የተመዘበሩ የህዝብና የመንግስት ሀብቶችን የፍትሀብሄር ክስ በመመስረት የማስመለስና የሚወረሱ ንብረቶችንም በህግ አግባብ የማስተዳደርና ለመንግስት በተገቢዉ ሁኔታ ገቢ ስለመሆናቸዉ ያረጋግጣል፡፡ የመንግስት መ/ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በሚያቀርቡ ጥያቄዎች መሰረት የውል ማርቀቅ እና ማጽደቅ ሥራ ይሰራል በተለይም ትላልቅ የመንግስት ፕሮጀክቶችን የውል ዝግጅት እና ድርድር ያደርጋል፤ የሕዝብና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም ይጎዳል ብሎ ሲያምን የመግባቢያ ሰነዶች ዝግጅትና ድርድር ያደርጋል፣ ያማክራል፡፡

