የዳይሬክቶሬቱ ተግባራት፡-
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የታክስና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በወንጀልና ፍ/ብሔር ዘርፍ ሥር የሚገኝ የሥራ ክፍል ሲሆን በዋናነት ከታክስ እና ግብር ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን፣ የጉምሩክ ወንጀሎችን እና ሌሎች መሰል በክልል እና ሀገር ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ልዩ ልዩ ኢኮኖሚክ ነክ ወንጀሎችን ምርመራ በመምራት፣ በፈጻሚዎች ላይ ተገቢውን የወንጀል ክስ በማቅርብ እና የህዝብና መንግስት ጥቅም አስጠብቆ በመከራከር አጥፊዎች በህግ የተቀመጠውን አስተማሪ ቅጣት እንዲቀጡ የሚሠራ እና ተጠያቂነትን በህግ አግባብ የሚያረጋግጥ ዳይሬክቶሬት ሲሆን ከድህረ ውሳኔ በኻላ ይግባኝ እና ሰበር ክርክሮችን የሚፈጽም ነው፡፡ በተጨማሪም በታክስና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት በተለይ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ማዘጋጀትና መስጠት፤ በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ ህጋዊ ምላሽ የሚሰጥ ዳይሬክቶሬት ሲሆን አደረጃጀቱም ከክልል እስከ ዞን ፍትህ መምሪያዎች ነው።

