Bureau Head message

ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ የተላለፈ መልዕክት

ለሕግ፣ ለፍትህ እና ለርትህ እንቆማለን! የሚል መሪ ቃል የቢሮውን ቁርጠኝነት የሚገልጽ  ሲሆን በክልላችን የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስኬታማ የሚሆነው የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ እና ዜጎች በፍትህ ተቋማት ላይ ሙሉ እምነት ሲኖራቸው ነው። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ይህንን ታላቅ አላማ አንግቦ “ለህግ፣ ለፍትህ እና ለርትዕ እንቆማለን!” በሚል መሪ ቃል ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።

Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!

  • ለህግ እንቆማለን!

ህግ የማህበረሰባችን የውል ስምምነት ነው። እያንዳንዱ የክልላችን ነዋሪ በህግ ፊት እኩል መሆኑን በማረጋገጥ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የመጠበቅ እና ህገ-ወጥነትን የመከላከል ስራችንን በቆራጥነት እንቀጥላለን። ህግ የማይነካው ግለሰብም ሆነ አካል እንዳይኖር በማድረግ የህግ የበላይነትን እናሰፍናለን።

  • ለፍትህ እንቆማለን!

ፍትህ ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት መድረስ ያለባት መሰረታዊ መብት ናት። ቢሯችን የፍትህ አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊ፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ በማድረግ በፍትህ እጦት የሚንገላቱ ዜጎች እንዳይኖሩ በትጋት ይሰራል። በተለይም ለሴቶች፣ ለህጻናት እና ለተጎጂ ክፍሎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ፍትህ በደጃቸው እንድትገኝ እናደርጋለን።

  • ለርትዕ እንቆማለን!

ርትዕ  ከህግ ቃላት ባለፈ የሞራል እና የፍትሃዊነት ጥያቄ ነው። እውነትን መሰረት ያደረገ፣ ከአድልዎ የጸዳ እና ለህሊና የታመነ ውሳኔ እንዲሰጥ በየደረጃው ያሉ የፍትህ አካላትን አቅም እንገነባለን። የህዝባችንን የሰላም እና የፍትህ ፍላጎት የሚያረካ የርትዕ ስራ መስራት የቢሯችን ዋነኛ መለያ ነው።

በመጨረሻም፣ በክልላችን የህግ የበላይነት እንዲከበር እና ፍትህ እንዲሰፍን የፍትህ አካላት፣ የጸጥታ መዋቅሩ እና መላው የክልላችን ህዝብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሬዬን አቀርባለሁ።

ለህግ፣ ለፍትህ እና ለርትህ በጋራ እንቆማለን!