ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፍትህ ቢሮ የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ መልዕክት፤
Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!Thank you for reading this post, don't forget to subscribe!የዜጎችን ሰላምና ህጋዊ መብት ለማስከበር በቁርጠኝነት እንሰራለን!
የወንጀልና የፍትሐብሔር ዘርፍ የቢሯችን ዋነኛ የክዋኔ (Core Process) ማዕከል እንደመሆኑ መጠን፣ በክልላችን የህግ የበላይነት እንዲሰፍንና ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የማድረግ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት ዘርፍ ነው።
በወንጀል ረገድ፦
ወንጀልን የመከላከልና ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ስራችን የክልላችንን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው። የወንጀል ምርመራና የክስ ሂደት ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊ እና ከማንኛውም አድልዎ የጸዳ እንዲሆን በትጋት እንሰራለን። በተለይም የሴቶችና ህጻናት ጥቃትን፣ የሙስና ወንጀሎችንና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን። ዓላማችን ጥፋተኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ፣ ተጎጂዎች ደግሞ ተገቢውን ካሳና ፍትህ እንዲያገኙ ማድረግ ነው።
በፍትሐብሔር ረገድ፦
የመንግስትንና የህዝብን የፍትሐብሔር ጥቅም ማስከበር፣ እንዲሁም የዜጎች ህጋዊ መብቶችና ግዴታዎች እንዲከበሩ ማድረግ የዘርፋችን ትኩረት ነው። የመንግስት ንብረትና ገንዘብ እንዳይባክን በህግ ከመከላከል ጀምሮ፣ ውሎችንና ህጋዊ ሰነዶችን በጥንቃቄ በመመርመር የክርክር ስጋቶችን እንቀንሳለን። በተጨማሪም፣ ዜጎች አለመግባባቶቻቸውን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ እንዲፈቱ የህግ ድጋፍና ምክር እንሰጣለን።
ዘርፋችን አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ፦
* የዐቃቤ ህግ ሙያዊ ስነ-ምግባርን ማጠናከር፤
* የክስ ጥራትንና ፍጥነትን ማሳደግ፤
* የዜጎችን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በማስጠበቅ ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል።
የክልላችን ህዝብ ለፍትህ አካላት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያችንን እያቀረብን፣ እኛም “ለህግ፣ ለፍትህና ለርትህ” የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን።
ፍትህ ለሁሉም!

አቶ ጤናሁን ጨረቆስ ዘቶ
የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ
